በጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የትም/ምዘና ጥናትና የፈተና ዝግጅት አስ/ር
ዳይሬክቶሬት ለወረዳ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ለትምህርት አመራሮችና
ለትም/ቤት መምህራን በፈተና ቢጋር አዘገጃጀት ዙሪያ የተዘጋጀ የገንዛበ
ማስጨበጫ ስልጠና
ታክሳስ 2017 ዓ.ም
አርባምንጭ
የስልጠና ሰነድ ዋናዋና ይዘቶች
መግቢያ
የትምህርት ምዘና ምንነት/ትርጉም
የምዘና ዓላማዎች
በፈተና ዕቅድና ዝግጅት ወቅት ትኩረት የሚሹ ጉዳዬች
1. የምዘናውን ዓላማ መወሰን
2. የሚለኩትን የመማር ውጤቶች መለየት
3.የትምህርት ውጤቶችን መግለጽ
4.የሚለካውን የትምህርት ይዘት መዘርዘር
መሠረታዊ የፈተና ባህርያት
የምዘና እቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ማዘጋጀት (TABLE OF SPECIFICATION)
የምርጫ ጥያቄ አይነቶች፡ጥንካሬ፣ድክመት፣ የጥያቄና አማራጮች ማዘጋጃ መመሪያዎች
መግቢያ
• የአንድ ሀገር ሥርዓተ ትምህርት በተፈለገዉ አቅጣጫ እየተከናወነ መሆኑንና አጠቃላይ
የትምህርቱ ዓላማ ግብ መምታቱን ለማረጋገጥ ከምንጠቀምባቸዉ ስልቶች አንዱ ፈተና
ወይም የትምህርት ምዘና ነዉ።
• የትም/ምዘና ዋና ዓላማ በየእርከኑ ወይንም በየደረጃዉ ተመጥኖ የተዘጋጀዉን የሥርዓተ
ትምህርት ይዘት በወቅቱ መጠናቀቁን በዚህም ተማሪዎች ተገቢዉን ዕዉቀትና ክህሎት
በመጨበጥ የባህርይ ለዉጥ ማምጣታቸዉን ለመለካት የምንጠቀምበት የመማር
ማስተማር ሂደት አካል ነዉ።
• የክፍል ፈተና በሚዘጋጅበት ወቅት ሥርዓተ ትምህርትን መሠረት በማድረግ በየትምህርት
ዓይነቱ በመርሀ-ትምህርት/Syllabus/ ዉስጥ ባሉት ይዘቶች/ምዕራፎች፣ ርዕሶችና ንዑሳን
ርዕሶች በዝርዝር ዓላማዎች ላይ ተመሥርቶ ከተማሪዎች የሚጠበቁ የዕዉቀት፣ የክህሎትና
የባህርይ ለዉጦችን ልለካ በምችል መልኩ የጥያቄ ስፐሲፊኬሽን ዝግጅት ይካሄዳል።
…የቀጠለ
በዚሁ መሠረት በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ክፍል መማሪያ መፅሐፍት ይዘት ተለይቶና
ተመጥኖ በተዘጋጀዉ ካሪኩለም/ይዘት ስፔሲፊኬሽን እንደ ዝርዝር የዕዉቀት ዘርፉና
የክፍለ ጊዜ ድልድሉ መሠረት ምን ያህል ጥያቄ እንደሚወጣ የሚገልጽ መዘርዝር
ይዘጋጃል።
ከዚህ አንጻር አዘጋጅ መምህራን የፈተና አዘገጃጀት ሥርዓትና መርሆዎችን አዉቀዉ
በጥንቃቄ እንዲያዘጋጁ ለማድረግ የትምህርት አመራሩም ሆነ ባለሙያው በአዘገጃጀቱ
ዙሪያ የጠራ ግንዛበ አንዲይዝና አውቀው እንዲመራ አቅጣጫ የሚያሳይ የክፍል ፈተና
ቢጋር አዘገጃጀት ዙሪያ እየተፈጠሩ ያሉ ክፍተቶችን ለማጥበብ ይህ ስልጠና ሰነድ
ተዘጋጅቷል። ሰነዱ በዉስጡ የፈተና ጥያቄ አዘገጃጀት እና የፈተና ጥያቄዎች ዓይነት
እንዲሁም ሌሎችንም ቴክኒካል ነጥቦችን አካቶ ይዟል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ
በምዘና ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርጉ የትምህርት አመራራሮችና ባለሙያዎች መምህራን
ፈተና ሲያዘጋጁ መሠረታዊ የፈተና ዕቅድ(Table of Specification) አዘገጃጀት ላይ
ግንዛቤ ኖሯቸው በስታንዳርዱ መሠረት ጥራቱን የጠበቀ ፈተና እንዲያደርጉ ለማስቻል፡፡
የትምህርት ምዘና ማለት ምን ማለት ነዉ?
የትምህርት ስርዓትን በተመለከት ውሳኔ ለመስጠት መረጃ የሚሰበሰብበት ሂደት ነዉ፡፡
የተማሪዎችን ውጤት (ተግባር) በጥንቃቄ በተሰበሰበ መረጃ ላይ ተመስርቶ
የመመርመር፣ የመተንተንና የመተግበር ሥራ ነው፡፡
ስለ ካሪኩለምና መርሃግብር ፤ስለመምህራን የትምህርት አሰጣጥና የተማሪዎች የትምህርት
አቀባበል፤ስለትምህርት ፖሊስ ለመወሰን የሚያስችል መረጃ የመሰብሰብ ሂደት ነዉ፡፡
ምዘና የማያርጥ ሂደት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ማለት በተከታታይ ምዘና፣በሚድ በሴ/ር፤በዓመት
ማጠቃላይ ፤በሦስት ዓመት፤በትምህርት እርከን ማጠቃላይ ለምሳሌ በ1ኛ ደረጃ /በሁለተኛ
ደረጃ ማጠናቀቂያ ሊሰጥ ይችላል፡፡
በአጠቃላይ ተማሪዎች ተገቢዉን ዕዉቀትና ክህሎት መጨበጣቸዉን እንዲሁም መምህራን
በአግባቡ ማስተማራቸዉን ለማረጋገጥ የሚደረግ መረጃ መሰብሰቢያ ሂደት ነዉ፡፡
የምዘና ዓይነቶች
ሂደታዊ ምዘና ;-ተከታታይ ምዘና ሲሆን የማስተማሩን ሥራ ለማሻሻልና ተቀባይነት ያለው
እንዲሆን ከመፈለግ የተነሣ የክፍል ውስጥ መልስ ማየትና ምልከታን የማስተማር ሂደት አካል
አድርጎ ይቀበላቸዋል፡፡
የማጠቃለያ ምዘና በልዩ ሁኔታ የአንድን የማስተማር ፕሮግራም ዓመታዊ ሥራ ሲጠናቀቅ
ውጤታማነትንና አገልግሎቱን የመገምገም ወይም አንድ የማስተማር ደረጃ ሲገባደድ በቅድሚያ
በተወሰነ ጊዜ የተማሪ ብቃት ላይ ዳኝነት ለመስጠት መረጃ መሰብሰቢያ ሂደት ነዉ፡፡
ተማሪዎች ምን እንደሚያውቁና መስራት እንደሚችሉ ለማረጋገጥ፣ የትምህርት
ግቦች ላይ መድረስ አለመድረሳቸውን ለማሳየት እና አልፎ አልፎ ከሌሎች ጋር በማወዳደር
ተማሪዎች የት ላይ እንዳሉ ለማሳየት ያገለግላል (Stiggins, 2002; Black and Wiliam,
1999) ፡፡
የምዘና ዓላማዎች
ውጤት ለመስጠት
የተማሪዎችን የስራ ክንውን በምስክር ወረቀት ለማረጋገጥ
ተማሪዎችን ለመምረጥ
ተማሪዎችን ለመመደብ
ለመምራትና ለማማከር
የአስተዳደራዊ የፖሊሲ ውሳኔዎች ለመስጠት
የፕሮግራም ምዘና ውሳኔዎች
የፈተና ዕቅድ አስፈላጊነት
የፈተና ዕቅድ ማለት (It is known as Test blue print) የፈተና ጥያቄዎች ከመዘጋጀታቸዉ
በፍት ታሳቢ ሊሆን የሚገቡ ቅድመ ፈተና ዝግጅቶችን ተጨባጭና ግልጽ በሆነ መልክ
የሚታቀድ ነዉ፡፡ሆኖም በርካታ መምህራን ምዘናዎችን ያለ ዕቅድ ማዘጋጀታቸዉና
መፈተናቸው በተማሪዎች ውጤት እና በትም/ት ፖሊሲ አተገባር ላይ አሉታዊ ተጽኖ አለዉ፡፡
በመሆኑም ምዘናዎችን ከማካሄዳችን በፊት ማቀዳችን የሚከተሉ ጠቀሜታዎች ያስገኛል፡-
ተማሪዎች የተማሩትን የትም/ት ይዘት ሽፋን ለይተን እንዲናዉቅ ያግዘናል፤
የትም/ት ይዘቶች ለማስተማር የወሰዱት ክ/ጊዜ ብዛት፤
የትም/ቱን አጠቃላይ እና ዝርዝር ዓላመዎችን መጠንና ዓይነት እንዲናዉቅ ያግዘናል
የተማሪዎችን ዕድሜ እና የዕዉቀት ደረጃ ያገናዘቡ ጥያቄዎችን እንዲናወጣ ያግዘናል
ይዘቱ ከወሰደዉ ክ/ጊዜ አንጻር ተመጣጣኝ ፣ተገቢ እና ጥራት ያለዉን ፈተና እንዲናወጣ
ይረዳናል፡፡
ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ካጠናቀቁ በኋላ ማሳየት የሚገባቸዉን የዕዉቀት፣ክህሎት እና
የባህር ለዉጦችን ለይተን እዲናዉቅ ይረዳናል
የምዘና መሳሪያዎች (ፈተናዎች) ዕቅድና ዝግጅት
የፈተና ጥያቄ አዘጋጆችና መምህራን በጽሁፍ ምዘና መሳሪያዎች
እቅድ ወቅት ተከታታይነት ያላቸው እርምጃዎችን ይጠቀማሉ፡፡
1. የምዘናውን ዓላማ መወሰን
የምዘና መሳሪያዎችን በመማር ማስተማር መርሃግብር ውስጥ
1/አንድን ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል እውቀትና ክህሎት
ለመመዘን (የምደባ ምዘና)፣
2/የመማር መሻሻልን ለመከታተል (ሒደታዊ ምዘና)፣
3/የመማር ችግርን ለመመርመር (ምርመራ ተኮር ምዘና)ና
4/የተማሪዎችን ችሎታ/ክንዋኔን ትምህርቱ ሲጠናቀቅ ለመለካት
(አጠቃላይ ምዘና) እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ የምዘና
መሳሪያ ዓይነት ከዓላማው አንፃር እንዲጣጣም ለማድረግ በንድፉ ላይ
ጥቂት ማሻሻያ ይፈልጋል፡፡
…የቀጠለ
2.የሚለኩትን የመማር ውጤቶች መለየት
የመማር ውጤቶች ከአጠቃላይ የትምህርት ዓላማዎች የሚመነጩትንና
ተማሪዎች በትምህት መጨረሻ ላይ ይደርሱባቸዋል ተብለው የሚጠበቁ
ውጤቶች መግለጫዎች ናቸው፡፡ ሁሉንም የሚያካትት ዝርዝር የትምህርት
ዓላማዎች ለማዘጋጀት ጠቃሚው መመሪያ የትምህርት ዓላማዎች ምደባ
(Taxonomy of Educational Objectives) ነው፡፡ ይህ የትምህርት
ዓላማዎች ምደባ ሁሉንም የሚጠበቁ የትምህርት ውጤቶችን ለመለየትና
ለመመደብ ይረዳል፡፡ እነዚህም ዓላማዎች በሚከተሉት ሶስት ዋና ዋና ዘርፎች
ሊመደቡ ይችላሉ፡፡
የትምህርት ዓላማዎች ምደባ
2.የዝንባሌ
ዘርፍ
(Affective
Domain)
የግንዛቤ ዘርፍ
( Cognitive
Domain )
እውቀት(Kn
owledge)
መረዳት/
መገንዘብ(C
omprehensi
on
መተግበር/
ትግበራ(Ap
plication)
Analysis,
Synthesis,
and
Evaluation,
)
የክህሎት ዘርፍ
(Psychomoto
r Domain)
የቤተ-ሙከራ
የተግባር
የመግባባት
የማስላት
የማህበራዊ
…የቀጠለ
1. የግንዛቤ ዘርፍ/ ( Cognitive Domain )
ይህ የእውቀት ዘርፍ ቀላል እውቀት (Simple Knowledge)
ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ተማሪዎች ለሚጠየቁት ነገር አንድና
ቀላል ምላሽ የሚሰጡት ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ከተማሪዎች
የሚጠበቅ ዋነኛ ጥረት የተማሩትን ነገር በመሸምደድ ያንኑ ፍሬ
ነገር እያስታወሱ ( Memorization) መስራት መሆኑ ታውቆ
ይህንን መመዘን የሚያስችሉ ጥያቄዎች ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
…የቀጠለ
ሀ.እውቀት(Knowledge) አንድን ነገር መረዳት፤መጠቀም ወይም መለወጥ ባይቻልም ማስታወስ መቻል
ስያሜዎች
 ዝርዝር እውነታዎች
ጽንሰ ሃሳቦችና መርሆዎች
ለ. መረዳት/መገንዘብ(Comprehension)፤-አንድን ነገር ከሌላ ከምንም ነገር ጋር ሳይዛመድ(ሳይነፃፀር)
የተላለፈዉን መልዕክት መገንዘብ
ጽንሰ ሃሳቦችና መርሆዎች ዘዴዎችና የአሰራር ሂደቶች
የጽሁፍ ማቴሪያሎች፣ግራፎች፣ካርታዎችና በቁጥር የተገለፀ መረጃ
የችግር ሁኔታዎች
ሐ. መተግበር/ትግበራ(Application)፡-አስፈላጊ በሆነበት ሁኔታ አጠቃላይ ግንዛቤን በመጠቀም ችግሮችን
መፍታት፤የተማሩትን ነገር በአድስና ተጨባጭ ሁነታ ላይ መጠቀም፤
ተጨባጭ መረጃ ጽንሰ ሃሳቦችና መርሆዎች
ዘዴዎችና የሥራ ሂደቶች ችግር የመፍታት ክህሎት
….የቀጠለ

ከፍተኛ የአስተሳሰብ ደረጃ የሚጠይቁ ክህሎቶች(መተንተን፣
ማቀናበርና መገምገም) (Analysis, Synthesis, and Evaluation,)
 በጥልቀት ማሰብ ችግር መፍታት

 አስተሳሰብ  አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር

2.የዝንባሌ ዘርፍ (Affective Domain)
ይህ ዓላማ የተማሪዎች ዝንባሌ፣ ፍላጎት፣ ምኞች፣ ምርጫ፣ ወዘተ መቀየር ማስቻሉን ወይም
ደግሞ ተማሪዎች ያመኑበትን፣ የወደዱትን ነገር፣ ዋጋ የሰጡትን ጉዳይ ሳያወላውሉና
ሳያቋርጡ በስራ ላይ ማዋላቸውን የሚያመላክት ሲሆን መምህራን በዚህ መልክ
ተረድተው በምዘና ወቅት ተግባር ላይ ማዋል አለባቸው፡፡
….የቀጠለ
ሀ. ዝንባሌዎች(Attitudes )

ማህበራዊ ዝንባሌዎች ሣይንሳዊ ዝንባሌዎች

ለ. ፍላጎቶች(Interests )
የግል ፍላጎቶች  ትምህርታዊ ፍላጎቶች
የሙያ ፍላጎት
ሐ. አድናቆቶች(Appreciations )

ስነጽሁፍ፣ ጥበብና ሙዚቃ  ማህበራዊና ሳይንሳዊ ስኬቶች
መ. ማስተካከሎች(Adjustments )

ማህበራዊ ማስተካከሎች  ስሜታዊ ማስተካከሎች
….የቀጠለ
3. የክህሎት ዘርፍ (Psychomotor Domain)
ይህ ዓላማ ተማሪዎች በአእምሮአቸው የያዙትን ነገር የአካል ክፍሎችን
በመጠቀም ችሎታቸውን (skills) በስራ ላይ ማዋልን ይመለከታል፡፡
ተማሪዎች እጅና አእምሮን በማቀናጀት በተግባር ሰርተው የሚያሳዩት
ነገር በክህሎት ዘርፍ በመጠቀም እንደሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
የቤተ-ሙከራ ክህሎት
የተግባር ክህሎት
የመግባባት ክህሎት
የማስላት ክህሎት
የማህበራዊ ክህሎት
Some list of Action Verbs in Learning Outcomes
3. የትምህርት ውጤቶችን መግለጽ
የመማር ውጤቶችን የመጠቀም ዋነኛው ምክንያት ተማሪው/ዋ ሊያሳይ/ልታሳይ የሚገባውን
የመማር ብቃቶች በመለየት የተወሰነውን ክህሎት ወይም የተቀመጠውን እውቀት ማወቅ
አለማወቁን/ቋን ለማረጋገጥ ነው፡፡
ጠቃሚ የትምህርት ውጤቶች የሚመነጩት
ከእውቀት ዘርፍ (የአእምሮ ክህሎቶች፣ እውቀት ወይም አስተሳሰብ)፣
ስሜታዊ ዘርፍ (በኃይለ-ስሜት መጎልበት፣ አመለካከት)ና
ከክህሎት ዘርፍ (የአንድ ነገር አሰራር መመሪያ፣ አካላዊ ክህሎት/ድርጊቶች) ነዉ፡፡
እነዚህ ዓላማዎች ዝርዝር፣ የሚለኩ፣ ተጨባጭ፣ ጠቃሚና ውጤት ተኮርና በተወሰነ የጊዜ ገደብ
የሚተገበሩ መሆን ይገባቸዋል፡፡
4. የሚለካውን የትምህርት ይዘት መዘርዘር
የትምህርት ውጤቶች ተማሪዎች የትምህርቱን ይዘቶች እንዴት ሊተገብሩ እንደሚችሉ
የሚወስኑ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የተማሪዎችን ባህሪና ዝርዝር የትምህርት ይዘትን
በተመሳሳይ ዓረፍተ ነገር መግለጽ ቢቻልም፣ ብዙ ጊዜ ለየብቻቸው መዘርዘር አስፈላጊ
ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ተማሪው/ዋ ለብዙ የተለያዩ የትምህርቱ ይዘት ክፍሎች በተመሳሳይ
መንገድ ምላሽ ሊሰጥ/ልትሰጥ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ተማሪው/ዋ በበርካታ የተለያዩ
መንገዶች ለአንድ የይዘት ክፍል ምላሽ ሊሰጥ/ልትሰጥ ይችላል/ትችላለች፡፡
ለምሣሌ፡- ተማሪው/ዋ፡- “ ” “
ስያሜን በራሱ አባባል ይገልፃል ፣ ውስን እውነታዎችን
” “ ”
ያስታውሳል ወይም የመርህ ምሳሌ ይሰጣል ብለን ብንገልጽ፤ እነዚህ ባህሪያት
በየትኛውም የትምህርቱ ይዘት ክፍል ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ፡፡
መሠረታዊ የፈተና ባህርያት
 ፈተና ሲዘጋጅ አምስቱ የፈተና ባህርያት በጥንቃቄ መታየት አለባቸዉ። እነዚህም፦
1/ የፈተና አስተማማኝነት /Reliability/፦ ከተማሪዎቹ ዕድሜና የክፍል ደረጃቸዉ
አንጻር እና የትም/ዓላማዉን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ምዛናዊ የሆነ አስተማማኝ
ፈተና
2/ የፈተና ተጨባጭነት/Objectivity/፦ግልጽ የሆኑና ተማሪዎች
በተማሩት ይዘቶች ላይ የተመሠረቱ ጥያቄዎችን ያካተተ፣
………..የቀጠለ
3/ የሚዘጋጀዉ ፈተና ጎበዙን ተማሪ ከደካማው መለየት የሚችል /A test
with discriminating Power/
4/ የፈተናዉ ተመጣጣኝነት / Level of Difficulty /፦ በጣም ያልከበደና
በጣምም ያልቀለለ ለደረጃዉ የሚመጥን ፈተና፣
5/ ከተማሪው የሚፈለገዉን የዕዉቀት ደረጃ የመለካት ብቃት
/Validity/ያለው፦ ለደረጃዉ የተቀመጠዉን ፕሮፋይል የሚያሟላ ፈተና
መዘጋጀት እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል
በዚህ መሠረት የማጠቃለያም ሆነ የክፍል ፈተና ጥያቄዎች ሲዘጋጁ 6 ዋና ዋና የዕውቀት
ዘርፎችንና/cognitive domains/ በዕውቀት ዘርፍ ሥር ያሉትን ንዑሳን ዘርፎችን
ማለትም
በስፔሲፊኬሽን የጥያቄዎቹን ብዛት፣ ከክፍለ ጊዜ ፣ ከክብደትና ቅለት አንጻር መዋቀሩን እርግጠኛ መሆን፣
ይህም ማለት በ Bloom’s Taxonomy of Behavioral Dimention መሰረት
መሰራቱን ማረጋገጥ
እነሱም፡ -እውቀት /Knowledge/
- አንብቦ መረዳት/መገንዘብ /Comprehension/
-ትግበራ /Application/
- ትንተና/ Analysis/
- ማዋቀር /Synthesis/
-ግምገማ/ Evaluation /ናቸው
ለዞናዊ ፈተና በወጥነት የሚዘጋጅ ሞዴል ፈተናም ሆነ ለማንኛውም የክፍል ፈተና አዘገጃጀት
ተማሪዎች በዝቅተኛው የትምህርት ቅበላ መሟላት ከሚጠበቅባቸው ፕሮፋይል አንፃር የሚታይ መሆን
አለበት፡፡
………….የቀጠለ
በመሆኑም የፈተና አዘገጃጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመጣው ከተፈታኞች ብዛት አንጻር
እርማት እንዲያመችና የተማሪዎችን ውጤት በወቅቱ በመግለጽ ትምህርት ለማስጀመር
እንዲቻል የፈተና አዘገጃጀቱ ሁሉንም የፈተና ዓይነቶችን ከማካተት ይልቅ አማራጮችን
ያካተቱ ጥያቄዎችን ( Multiple choice Questions) ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል
ተደርጎ ተግባራዊ እየሆነ ቆይቷል፡፡
የምዘና እቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ማዘጋጀት (TABLE OF
SPECIFICATION)
የምዘና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ የፈተና ዕቅድ በመባል ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ
የምዘና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ዓላማዎች የምዘናን ጥያቄዎች ከሚከተሉት
ጉዳዮች ጋር ማቀናጀት ነው፡፡ እነሱም፡
ማንኛውንም የይዘት ክፍል ለማስተማር የሚወስደው ጊዜ፣
በተማሩት የትምህርት ዓይነት የመማር ብቃት፣
በብቃቶቹ ወይም በተቀመጡት መስፈርቶች የሚፈለገው የአስተሳሰብ ደረጃ፣
በምዘና ውስጥ ምን እንደተካተተና ይዘቱም ከተቀመጡት መስፈርቶች ጋር
መዛመዱን ማወቅና
የምዘናውን ጥያቄዎች ጥራት መጨመር ናቸው፡፡
…የቀጠለ
በመቀጠል ተማሪዎቹ ለእያንዳንዱ የይዘት ክፍል ምን ምን የባህሪ ለውጥ
እንደሚያሳኩባቸው በዕውቀት ዘርፍ ደረጃዎች መወሰን፡፡
ለምሳሌ ምን ያህል ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማቴሪያሉን ተረድተውታል?
ተማሪዎች በሂደት ውስጥ ያለውን ተገቢ ተግባር መለየት (እውቀት)፤
ጽንሰ-ሃሳቦችን በራሳቸው አባባል ማብራራት(መረዳት)፤
መርህን ወይም ሂደትን በአዲስ ሁኔታ ውስጥ ስራ ላይ ማዋል (መተግበር)
የእቅድ ዝርዝር ክፍሎችን ማወዳደርና ማነፃፀር (ትንተና)፤ ወይም ችግርን ለመፍታት
እቅድ ማቀድ (ማቀነባበር)ይችላሉን?
የፈተናውን ጥያቄ ብዛት መሠረት በማድረግ ከየይዘቱ የሚወጡ ጥያቄዎችን
ለማስተማር ከወሰደው ክፍለ ጊዜ አንፃር በመቶኛ ማስላት ያስፈልጋል
…የቀጠለ
የጥያቄ ብዛት መወሰን የሚያስችል ቀመር
የጥያቄ ብዛት= የክፍለ ጊዜ ብዛት x ጠቅላላ የጥያቄ ብዛት
አጠቃላይ ክፍለ ጊዜ ብዛት
የፈተና ጥያቄዎች ብዛት ሲወሰን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው
ጉዳይ ሁሉም ተማሪዎች ፈተናውን እንዲጨርሱ በቂ ጊዜ
መሰጠት እንዳለበት ነው፡፡ ጥያቄው ከቀላል የማስታወስ ችሎታ
በላይ የሚለካ ከሆነ ቢያንስ አንድ ደቂቃ መስጠት ይገባል፡፡
…የቀጠለ
የፈተና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ዝግጅት አሰራር ቅደም ተከተል በሚቀጥሉት ሁለት እንደ አርአያ
በተወሰዱ ምሳሌዎች በሁለት ሠንጠረዥ ቀርበዋል፡፡
የፈተና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ምሳሌ
የትምህርት ቤቱ / የተቋሙ ስም፡- ---------
የትምህርት ዓይነት፡- ---------
የክፍል ደረጃ፡- ------------
የፈተናው ዓላማ፤-
ሀ) ተማሪዎቹ በትምህርት ያመጡትን የባህሪ ለውጥ ለመመዘን
ለ) በትምህርቱ ተማሪዎች ያሳዩትን የመማር መሻሻል ለመከታተል
ሐ) በትምህርቱ የገጠማቸው የመማር ችግር ካለ ለመለየት
መ) በመማር-ማስተማር ስልቶች ላይ ግብረ መልስ ለማግኘት
የጥያቄዎችን መጠን አወሳሰን የሚያሳይ የፈተና ዕቅድ
ሠንጠረዥ 1/T/S/FOR DETERMINING THE PROPORTION ITEMS
Major and
Specific Content
areas
(ዓበይና ንዑስ ይዘቶች(ርዕሶች)
Period
Allotmen
t
Number of
questions in
relation
to period allotment
Number of
Questions
(%)
Formula for deciding the No of
questions
Number of periods X total items
Total number of periods
1. Rational numbers 32 30 100%
1.1 The concept of
Rational
9 8 28.1% Eg. 9 X 30 = 8.45 = 8
32
1.2 The order of Rational
numbers
7 7 21.8% Eg. 7 X 30 = 6.56 = 7
32
1.3 Operation of
rational numbers
1.3.1 Addition Rational
numbers
4 4 13% Eg. 4 X 30 = 4
32
1.3.2 Subtraction of Rational
numbers
3 3 10% Eg. 3 X 30 = 3
32
1.3.3 Multiplication of Rational
numbers
6 5 17% Eg. 6 X 30 = 5
32
1.3.4 Division of Rational
numbers
3 3 10% Eg. 3 X 30 = 3
32
የትምህርት ዓላማ መሠረት ያደረገ የፈተና ዕቅድ መመሪያ
ሠንጠረዥ 3 .የጥያቄ ዓይነትን መሠረት ያደረገ የፈተና ቢጋር
------- --የቀጠለ
የትምህርት ዘመን ----------------------------------
 የአዘጋጅ መ/ር ስም ------------------- ---ፊርማ ----------- ቀን ----------
 የድፓርቲ መንት ኃላፊ ስም---------------ፊርማ ------------- ቀን ------
የር/መ/ር ስም ----------------------- ፊርማ ----------- ቀን --------
ማሳሰቢያ ፡ - ይህ የፈተና ቢጋር የተዘጋጀው በ7ኛ ክፍል ሒሳብ በአንድ ምዕራፍ
ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀ ሲሆን መምህራን የፈተና ቢጋር ማዘጋጀት ያለባቸው
አስተምረው በሸፈኑት ምዕራፍ ላይ መሆን አለበት ፡፡
…የቀጠለ
በመቀጠል የጥያቄ ዓይነቶች ላይ መወሰነ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በትምህርቱ ዓላማዎችና
በሚለካው ይዘት ባህሪ ይወሰናል፡፡ በሠንጠረዥ ላይ የተገለፀው የፈተና ዕቅድ መመሪያ
ሠንጠረዥ ከይዘቱ ጋር የሚሄዱትን ተገቢ የጥያቄ አይነቶችን ለመወሰንም ይረዳናል፡፡
እዉነት /ሐሰት
አዛምድ
ባዶ ቦታ ሙላ
ምርጫ
አብራራ
የምርጫ ጥያቄ
የምርጫ ፈተና ጥያቄዎችን ማዘጋጀት የምርጫ ፈተና/ጥያቄ ምላሽ የሚፈልግ
ችግርንና አማራጭ መልሶችን አካቶ ይይዛል፡፡ ምላሽ የሚፈልገው ችግር
በቀጥታ ጥያቄ ወይም ባልተሟላ ዓረፍተ ነገር መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡
ምላሽ የሚፈልገው ችግር የጥያቄው ግንድ ሲባል እንደመፍትሔ ጥቆማ
በዝርዝር የተቀመጡት ደግሞ አማራጭ መልሶች በመባል ይታወቃሉ፡፡
ከቀረቡት አማራጭ መልሶች ውስጥ አንዱ ትክክለኛ መልስ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ
አሣሣች መልሶች በመባል ይታወቃሉ፡፡ አማራጭ መልሶቹ ቃላትን፣ ምልክቶችን፣
ቁጥሮችን፣ ሐረጎችን ወዘተ ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡
የምርጫ ጥያቄ አይነቶች፡
i. ዝግ ግንድ ጥያቄ (Closed stem)፡- ዝግ ግንድ ምላሸ
የሚያስፈልገውን ጥያቄ የሚያቀርብ ነው፡፡
ዓረፍተ ነገሩ የሚጠናቀቀው በጥያቄ ምልክት ነው፡፡
ምን እንደተጠየቀ ግልጽ በሆነ መንገድ ያስቀምጣል፡፡
አንባቢዎችን/ተፈታኞችን ወደ አማራጭ መልሶች ይመራቸዋል፡፡
አማራጭ መልሶቹ ስዕሎች፣ ዲያግራሞች፣ ሠንጠረዦች በሚሆኑበት ጊዜ
የጥያቄው ግንድ ዝግ መሆን አለበት፡፡
ምሣሌ፡- ከሚከተሉት ውስጥ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የቱ ነው?
…የቀጠለ
ii. ያልተገደበ ክፍት ግንድ ጥያቄ (Open stem)፡- ያልተሟላው ዓረፍተ ነገር
ከአማራጮቹ በአንዱ ይሟላል፡፡
አጠር ያለና ቀጥተኛ፤
ያልተገደበ ነው፡፡
አማራጭ መልሶቹ ከጥያቄው ግንድ ጋር በሰዋሰው ስርዓት ተስማሚ መሆን
አለባቸው፡፡
ምሣሌ፡- የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ------------- ነው፡፡
…የቀጠለ
ጠንካራ ጎኖች
የትምህርቱን ይዘት በስፋት መወከል ያስችላል፡፡
እርማቱ ቀላልና ተጨባጭ ነው፡፡
የጥያቄ ትንተናን ለማከናወን ይጠቅማል፡፡
የተማሪዎችን ችግር ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል፡፡
በሁሉም የትምህርት እርከኖች ላይ መጠቀም ይቻላል፡፡
ደካማ ጎኖች
oየመማር ውጤቶችን በቃል (በሐረግ) ደረጃ መለካት ላይ
የተወሰነ/የተገደበ ነው፡፡
oሃሳብን የማደራጀትና የማቅረብ ችሎታን አይለካም፡፡
o መልስ የሚመስል አሳሳች መልስ ማዘጋጀት/ማግኘት
አስቸጋሪ ነው፡፡
የምርጫ ጥያቄዎች ለማዘጋጀት የሚረዱ መመሪያዎች

እያንዳንዱ ጥያቄ ውስን ይዘትና አንድ ውስን የመማር ውጤትን/ዓላማን
ማንጸባረቅ አለበት፣

እያንዳንዱን ጥያቄ ለመማር ጠቃሚ በሆነ ይዘት ላይ እንዲመሠረት ማድረግ፤
የማይረባ ይዘትን ማስወገድ ያስፈልጋል፣

ከፍተኛ የመማር ደረጃን (higher level learning) ለመፈተን አዳዲስ ነገሮችን መጠቀም
ያስፈልጋል፣
የመማሪያ መጽሐፍ ቋንቋን ወይም በመማር ማስተማር ወቅት እንጠቀምበት የነበረን የቋንቋ
አጠቃቀም በቀጥታ እንዳለ ከመውሰድ ይልቅ ለወጥ ባለ መልክ በመጠቀም ጥያቄው ከቀላል
የማስታወስ ብቃት የተሻለ እንዲለካ ማድረግ፣
የእያንዳንዱን ጥያቄ ይዘት በሌላ ፈተና ጥያቄዎች ይዘት ላይ እንዳይመሠረት ጥንቃቄ ማድረግ፣
…የቀጠለ
የምርጫ ጥያቄ ሲዘጋጅ በጣም ውስንና በጣም አጠቃላይ ይዘትን ማስወገድ፣
አስተያየት ላይ የተመሠረቱ ጥያቄዎችን ማስወገድ፣
 ጥያቄዎች ሲዘጋጁ ጥቅም ላይ የሚውሉት ቃላት በተቻለ መጠን ለተፈታኝ
ተማሪዎች ቀላል እንዲሆኑ ማድረግ፣
ጥያቄዎቹ ከግድፈት የፀዱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እርማት ማከናወን ተገቢ ነው፣
 ትክክለኛ ሰዋሰው፣ ሥርዓተ ነጥብና የፊደላት አጻጻፍ (ሥርዓተ ሆሄያት) መጠቀምና
የእያንዳንዱን ጥያቄ ማንበቢያ ጊዜ ለመቀነስ በጣም ረጅም የሆኑ ጥያቄዎችን
ማስወገድ፡፡
የጥያቄ ግንዶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ መመሪያዎች
የጥያቄ ማዘጋጀት ግቡ ተማሪዎች ምን እንደሚያውቁና ማከናወን እንደሚችሉ ለመረዳት
እንጂ የሚሸውዱ ጥያቄዎችን ለማዘጋጀት አይደለም፡፡
የምርጫ ጥያቄ ግንዱን ስናዘጋጅ ልንከተላቸው የሚገቡ ጥቂት መመሪያዎች
የሚከተሉት ናቸው፡፡
የጥያቄውን ግንድ በጥያቄ መልክ ወይም ባልተሟላ ዓረፍተ ነገር መልክ መግለጽ
 የጥያቄ ግንድ ለመጻፍ ያልተሟላ ዓረፍተ ነገር የምንጠቀም ከሆነ የሚሞላውን ባዶ
ቦታ የዓረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ወይም መሀል ላይ አለማድረግ፣
የጥያቄው ግንድ ውስጥ ያለው ትእዛዝ ግልጽና የቃላት አጠቃቀሙም ተፈታኞቹን ምን እንደተጠየቁ
የሚያሳውቋቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
 እያንዳንዱ ጥያቄ ዝርዝር የመማር ውጤትን እንዲለካ ማድረግ፣
በጥያቄው ግንድ ውስጥ ከሚፈለገው በላይ ቃላትን ማጨቅ ማስወገድ፣
የጥያቄውን ግንድ በተቻለ መጠን በአወንታዊ አባባል መግለጽ፣ አሉታዊ አገላለጽን ማስወገድ
…የቀጠለ
ዋናውን ሃሳብ በጥያቄው ግንድ ውስጥ ማካተት፣
የጥያቄው ግንድ በተገቢው አገላለጽ ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ መግለጽ አለበት፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ በዓረፍተ ነገር
ውስጥ ሁልጊዜም ግስ እንዲካተት ማድረግ፣
ከፍተኛ የአስተሳሰብ ደረጃን ለመለካት የምርጫ ጥያቄን መጠቀም ይቻላል፣
 የምርጫ ጥያቄዎች ራሳቸውን ችለው መቀረጽ አለባቸው፡፡ ይህ ማለት የአንዱ ጥያቄ መልስ በሌላው ጥያቄ መልስ
ላይ መመስረት የለበትም፣
የተማሪዎችን የመረዳት፣ የመተግበር፣ የመተንተን፣ የመገምገምና የማስታወስ ችሎታዎችን የሚለኩ ጥያቄዎች ማዘጋጀት
ላይ ማተኮር፣
በጥያቄው ግንድ ውስጥ መካተት የሚገባቸውን ሁሉ ማካተት፡፡ በአማራጭ መልሶች ውስጥ ተመሳሳይ አባባሎችን
አለመደጋገም፡፡ ይህ የሚቆጥበው ጥያቄውን የመፃፊያ ጊዜ ብቻ ሳይሆን የተማሪዎችንም የማንበቢያ ጊዜ ነውStem:
Example In objective testing, the term objective:
A. refers to the method of identifying the learning outcomes.
B. refers to the method of selecting the test content.
C.refers to the method of presenting the problem.
D. refers to the method of scoring the answers.

በሚከተለው መልክ የሚጀምርና የማይገናኙ የአማራጮች ስብስብን የሚያስከትል ጥያቄ አለመጠየቅ፡፡
ይኸውም፡- “ከሚከተሉት ውስጥ እውነት/ሐሰት የሆነው የቱ ነው?” ስለዚህ በሚከተለው መልክ
“
የሚጀምርና ሁሉም አማራጭ መልሶች አንድ ጉዳይ ላይ X” የሚያተኩር ጥያቄ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡
“ “
ከሚከተሉት ውስጥ X”ን በተመለከተ እውነት/ሐሰት የሆነው የቱ ነው?”

የተሟሉ ዓረፍተ ነገሮች ላይ ትክክለኛ ስርዓተ ነጥብ መጠቀም

በአሉታዊ መንገድ የተገለፀ የጥያቄ ግንድ ግራ መጋባትን (መወናበድን)
ይፈጥራል፤ ስለዚህ መጠቀም አይገባም፡፡ በአሉታዊ መንገድ የተገለፀን የጥያቄ
ግንድ መጠቀም የግድ ከሆነና አሉታዊ ቃሉም አንድ ከሆነ፤ ትኩረት እንዲስብ ቃሉ
ሲፃፍ ጎላ የሚልበትን ስልት መጠቀም (ለምሳሌ፡ ከስሩ በማስመር ሊሆን
ይችላል)፣
……የቀጠለ
በጥያቄው ግንድ ውስጥ የምንጠቀማቸው ቃላት ከተፈታኞቹ የግንዛቤ ደረጃ ጋር
የሚመጣጠኑ መሆን አለባቸው፣
የጥያቄው ግንድ ሲዘጋጅ በጣም ውስን እውቀት ላይ ማተኮርን ማስወገድ፣
የጥያቄው ግንድ ሲዘጋጅ በቀጥታ ከተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ ላይ
መገልበጥንና አላስፈላጊ ቃላትን መጠቀምን ማስወገድ፣
 ተገቢውን ሰዋሰው፣ ስርዓተ ነጥብና የፊደላት አፃፃፍ ስርዓት በወጥነት
መጠቀምና
 የሚያሳስቱ ጥያቄዎችን ማለትም ተፈታኞች እንዲታለሉና እንዲሸወዱ በማድረግ
የተሳሳተ ምላሽ እንዲሰጡ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን ማስወገድ
አማራጭ መልሶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ መመሪያዎች

አማራጭ መልሶች ተቀራራቢ ርዝማኔ ያላቸውና የአፃፃፍ ዘይቤያቸውም ከትክክለኛው መልስ ጋር
ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ ትክክለኛው መልስ በርዝማኔው፣ በቃላቶች አጠቃቀምና በሌሎች አላስፈላጊ ነገሮች
ከአሳሳች መልሶች የተለየ መሆን የለበትም፡፡

በአጠቃላይ በፈተናው ውስጥ ትክክለኛው መልስ በሁሉም የመልስ አማራጮች መካከል መሰራጨት
አለበት “
፡፡ ይህም ማለት ” “ ” “ ” “
ሀ ፣ ለ ፣ ሐ ፣ ና መ” እንደ ትክክለኛ መልስ ተቀራራቢ ድርሻ እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

አንድ ብቻ ትክክለኛ/በጣም የተሻለ መልስ መኖሩን እርግጠኛ መሆን፣

አማራጭ መልሶች ለሌላ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ፍንጭ መስጠት የለባቸውም፣

ማዘጋጀት የሚቻለውን ያህል ውጤታማ አማራጭ መልሶችን ማካተት ቢቻልም ጥናቶች የሚመክሩት ከሦስት
እስከ አረት አማራጭ መልሶችን መጠቀም፡፡

እያንዳንዱ ጥያቄ አንድ ትክክለኛ መልስና ሶስት አሳሳች መልሶች ሊኖሩት ይገባል (ባለአራት አማራጮችን
የምንጠቀም ከሆነ )፣ አማራጭ መልሶች በግልጽነት ጉድለትና አሻሚነት የተነሣ ሊያሳስቱ ወይም ሊያደናግሩ
አይገባም፣
…የቀጠለ
አማራጭ መልሶች አንድ አይነት ትርጉም ሊኖራቸው አይገባም፡፡ አሳሳች መልሶቹ አንዱ ከሌላው
የተለየ ትርጓሜ ሊኖረው ይገባል፡፡ አሳሳች መልሶች አንድ አይነት መሆን የለባቸውም፡፡ አንድ ውስን ትርጉም
ያለው አሳሳች መልስ በሌላ አጠቃላይ ትርጉም ባለው አሳሳች መልስ ውስጥ መካተት የለበትም፣
“ ”
ሁሉም መልስ ናቸው “ ”
የሚለውን አማራጭ መልስ መጠቀም ማስወገድ፡፡ ሁሉም መልስ ናቸው
የሚለው አማራጭ መልስ የሚፈጥረው ችግር ጥያቄውን በጣም ቀላል ማድረጉ ነው፡፡ ተማሪዎች
“
ከቀረቡት አማራጭ መልሶች መካከል ቢያንስ አንዱ የተሳሳተ ምላሽ መሆኑን ካወቁ ሁሉም መልስ
”
ናቸው የሚለው ምላሽ ትክክለኛ መልስ እንደዳልሆነ በግልጽ ያውቁታል፡፡ በሌላ በኩል ከቀረቡት
“ ”
አማራጭ ምላሾች ውስጥ ሁለቱ ትክክል መሆናቸውን ካወቁ፣ ሁሉም መልስ ናቸው የሚለው ምላሽ
ትክክለኛ መልስ መሆኑን በቀላሉ ያውቁታል፡፡ ተማሪዎች ይህንን ፍንጭ በመጠቀም ፈጣን ምላሸ
ይሰጣሉ፣
 “ ”
ሁሉም መልስ አይደሉም የሚለውን እንደ አማራጭ መልስ መጠቀምን ማስወገድ፡፡ ይህን
አማራጭ መጠቀም የሚቻለው ፍጹም/ሙሉ በሙሉ ትክክለኛነትን መለካት በሚቻልበት ሁኔታ ብቻ ነው፡፡
ለምሳሌ እንደ ሂሣብ፣ ሰዋሰው፣ ስርዓተ ሆሄያት፣ ጂኦግራፊ፣ ታሪካዊ ቀናት፣ ወዘተ፡፡
…የቀጠለ
ያለበለዚያ ተማሪዎች ከአማራጭ መልሶቹ ውሰጥ አንዱን አማራጭ መልስ ትክክል ነው እያሉ ሊከራከሩ
ይችላሉ፣

ሁለት ወይም ሶስት አማራጮችን በአንድ አማራጭ የሚያካትት አማራጭ መልሶችን መጠቀም ማስወገድ
(ምሳሌ፡- ሀ ና መ፣ ሀ ና ሐ፣ ሀ፣ ለ ና ሐ፣ ወዘተ)፡፡

አማራጭ መልሶች በከፊል ትክክል የሆኑ አሳሳች መልሶችን አያካትቱም፡፡ (ለምሣሌ፡- ጥንድ አማራጭ
መልሶች ማለት አንደኛው አማራጭ መልስ ትክክለኛ መልስና ሌላኛው አማራጭ መልስ ትክክለኛ መልስ
ያልሆነ)፣
 ፍፁም መለያዎችን (Absolute qualifiers) ማስወገድ፡፡ ለምሳሌ፡- “ ” “ ”
ሁሉም ፣ ሁል ጊዜ ፣
“ ”
ፈጽሞ የመሳሰሉት ፍፁም መለያዎች ብዙ ጊዜ ትክክል ባልሆነ አማራጭ መልስ ውስጥ የሚገኙ
ናቸው፡፡ አንፃራዊ መለያዎችን (specific qualifiers) መጠቀምንም ማስወገድ ይገባል፡፡ ለምሳሌ፡- “ብዙ
” “ ” “ ”
ጊዜ ፣ በተደጋጋሚ ፣ አንዳንድ ጊዜ የመሳሰሉት ግልጽ ያልሆኑ ቃላትን አለመጠቀም፣
ከተቻለ አማራጭ መልሶችን ከጥያቄ ግንዱ ስር አግድም ከመደርደር ወደታች በረድፍ እንዲደረደሩ
ማድረግ ይመረጣል፣
ምን ያህል ቀላል፣ አማካይና ከባድ ጥያቄዎች እንደሚወጡ
በጥያቄዎቹ ላይ ሁከት ተሚፈጥሩና ተቀባይነት የሌላቸዉ
ስለ ብሄር
ሀይማኖት
ጾታ
ፖለቲካ
አካል ጉዳተኛነትን የሚያንኳስሱ ቃላቶች
አለመጠቀም
የፈተና ወረቀት ገጽ ሽፋን
በፈተና ወረቀቱ የፊትለፊት ሽፋን ላይ ፈተናውን የሚያስተዳድረው ባለቤት ሙሉ ስም፣
ፈተናው አይነት ፣ የጥያቄዎች ብዛት (Number of Items) እና ለፈተናው
የተሰጠው ጊዜ (Time Allowed) የመጀመሪያ ፊደላት ከ”of” በስተቀር ሌሎቹ
በትልቅ ፊደላት (capital letters) ይፃፋሉ፡፡ በተጨማሪም “hours” በሙሉ
በትንሽ ፊደላት (small letters) ይፃፋል፡፡
እንዲሁም የተሰጠው የፈተና ጊዜ በደቂቃ (Minutes) ሳይሆን በሰዓት (hours)
መፃፍ አለበት፣
ለምሣሌ 2:00 hours
የጥያቄዎችን አፃፃፍ (Items writing) ፡-
የፅሁፍ ፊደል መጠን (font size) -­
­14
የፅሑፍ ፊደል ዓይነት (font type) - በእንግሊዝኛ ለሚፃፉ ፈተናዎች Times New Roman
በየፅሑፍቹ መስመሮች መካከል የሚኖረው የቦታ ስፋት አንድ መስመር (single line space)
ይሆናል።
በጥያቄ ቁጥርና በጥያቄው መካከል ያለው ርቀት -­
­1.5
በጥያቄ ግንድና በአማራጮቹ መካከል ያለው ርቀት -­
­1.5
የምርጫ ፊደላት ሲፃፉ በትልቅ ፊደላት (capital letters) ተፅፈው ነጥብ
ይደረግባቸዋል፡፡
ምንባብ፣
ለእንግሊዝኛ፣አፍ መፍቻ ቋንቋና አማርኛ እያንዳንዱ አንቀፅ አጠር ያለ ሆኖ
ከ150 እስከ 200 ቃላት የያዘ መሆን አለበት
አመሰግናለሁ!

More Related Content

PPTX
professional devlopment training for teaching .pptx
PPTX
የእቅድ መመሪያ የገለፃ ሰነድ for different sectors
PPTX
Lifeskill.pptx - Last saved by user.pptx
PPTX
Table of Specification - Professional Education
PDF
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
PDF
ስልጠና ከመሰጠቱ በፊት የተደረገ የስልጠና ዳሰሳ ጥናት፣ እና ስልጠና ከተሰጠ በኋላ የስልጠና አሰጣጡ የእርካታ መለኪያ መጋ...
PDF
Business Plan Preparation and Vision Setting Final.pdf
PPTX
የማስተማር ዘዴ.pptx a presentation about the KMKC church
professional devlopment training for teaching .pptx
የእቅድ መመሪያ የገለፃ ሰነድ for different sectors
Lifeskill.pptx - Last saved by user.pptx
Table of Specification - Professional Education
20142022 berhanu training_education_development_need_assessment [read-only]
ስልጠና ከመሰጠቱ በፊት የተደረገ የስልጠና ዳሰሳ ጥናት፣ እና ስልጠና ከተሰጠ በኋላ የስልጠና አሰጣጡ የእርካታ መለኪያ መጋ...
Business Plan Preparation and Vision Setting Final.pdf
የማስተማር ዘዴ.pptx a presentation about the KMKC church

What's hot (20)

KEY
Examples of teaching philosophy and strategies
PDF
Classroom assessment manual amharic
PPTX
Curriculum development process
PPTX
curriculum foundation,design and development
PPT
National professional standards for teachers in pakistan
PPT
Models of teaching
PPT
INFLUENCE OF SOCIAL FACTORS ON EDUCATION .ppt
PPTX
Presentation1
PDF
Quality Assurance in Teacher Education: Trends and Challenges in India
PPT
Implications of Curriculum Changes
PPT
Curriculum Development
PDF
approaches to curriculum design
PPT
Curriculum development cycle
PPTX
Development in Education(Curriculum Development)
PPTX
Evaluating the curriculum
PPTX
School Plant Management Educ. 265
PPTX
Concepts of educational planning
DOCX
TEACHER SUPPORT CURRICULUM- DESIGNING TEACHER GUIDES, SUBJECT RESOURCE MODULES
PPTX
Outcomes Based Education
Examples of teaching philosophy and strategies
Classroom assessment manual amharic
Curriculum development process
curriculum foundation,design and development
National professional standards for teachers in pakistan
Models of teaching
INFLUENCE OF SOCIAL FACTORS ON EDUCATION .ppt
Presentation1
Quality Assurance in Teacher Education: Trends and Challenges in India
Implications of Curriculum Changes
Curriculum Development
approaches to curriculum design
Curriculum development cycle
Development in Education(Curriculum Development)
Evaluating the curriculum
School Plant Management Educ. 265
Concepts of educational planning
TEACHER SUPPORT CURRICULUM- DESIGNING TEACHER GUIDES, SUBJECT RESOURCE MODULES
Outcomes Based Education
Ad

Similar to ትምህርት ምዜ አዘገጃጄት ዜደ ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት ቤቶች.pptx (20)

PPTX
የማማከር እና የሱፐርቪዥን መጽሀፈ እድ text evaluation .pptx
PPTX
የማህደረ ተግባር አደረጃጀት- Portfiolio Preparation.pptx
PPTX
ሁሉን አቀፍ የሱፐርቪዥን ግብረ መልስ 2ኛ ዙር ጥር2017.pptx
PPTX
የማርየ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሱፐርቪዥን ግብረ መልስ.pptx
PPTX
sodo school improvement plane pp day 1.ppt
PPTX
Supevision Presentationqwertyuioqwe.pptx
PDF
BGREB-TELD-School Principals Efficiency.pdf
PDF
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdf
PDF
Ttlm data analisis doc3
PDF
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
PPTX
inspection for jiga.pptx
PDF
2013 berhanu training need assessment presentationi
PPTX
Reading Manual for grade ne up to four (2).pptx
PPT
Special Capacity Building Training Program for Secondary School Leadersrevise...
PDF
Tvet supervision 1
PPTX
62074819ddddddddffffd5-PPTM-E-3 (1).pptx
PDF
2 Training Managemen, Need Assessment, Training Maitedlogy and Evaluation rep...
PPTX
CTE CP Choices and class labelingbmh.pptx
PDF
action-research-manual-2 (1).pdf
PPTX
Curriculum_Reform_Presentation_ነሐሴ_2ዐ14_ለአጠልጣኞች_ሥልጠና_የተዘጋጀ_2.pptx
የማማከር እና የሱፐርቪዥን መጽሀፈ እድ text evaluation .pptx
የማህደረ ተግባር አደረጃጀት- Portfiolio Preparation.pptx
ሁሉን አቀፍ የሱፐርቪዥን ግብረ መልስ 2ኛ ዙር ጥር2017.pptx
የማርየ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሱፐርቪዥን ግብረ መልስ.pptx
sodo school improvement plane pp day 1.ppt
Supevision Presentationqwertyuioqwe.pptx
BGREB-TELD-School Principals Efficiency.pdf
EMD_2016_ብርሃኑ_የስልጠና_ፍላጎት_ዳሰሳ_Pawer_Pont presentation.pdf
Ttlm data analisis doc3
Education and Training for All ACTION RESEARCH ET -.pdf
inspection for jiga.pptx
2013 berhanu training need assessment presentationi
Reading Manual for grade ne up to four (2).pptx
Special Capacity Building Training Program for Secondary School Leadersrevise...
Tvet supervision 1
62074819ddddddddffffd5-PPTM-E-3 (1).pptx
2 Training Managemen, Need Assessment, Training Maitedlogy and Evaluation rep...
CTE CP Choices and class labelingbmh.pptx
action-research-manual-2 (1).pdf
Curriculum_Reform_Presentation_ነሐሴ_2ዐ14_ለአጠልጣኞች_ሥልጠና_የተዘጋጀ_2.pptx
Ad

More from eyaluayssa10q (15)

PPTX
1a. position papeEDUCATIONr and its concern.pptx
PPTX
Evidences_for_the_existence_of_the_changes_in_the_new_grade_10_Physics.pptx
PPTX
table of specification for teachers principals and educational leaders .pptx
PPT
2021 Education Sector Aanlysisof secondey and higher education MA.ppt
PPTX
hool-leadersrevised-drafCommunication and Interpersonal Skillst -presentation...
PPTX
TEXTBOOK PRINTING AND DISTRIBUTION IN SOUTHERN ETHIOIAPPT edited.pptx
PPTX
የትምህርት ስብራት ለመጠገን እኔም ድርሻ አለኝ የመማሪያ መፅሀፍት አቅርቦትና የት/ት ጥራት
PPTX
1 Physiology of Pregnan women Unit1-1.pptx
PPTX
Ayalueffects of transformational leadership on students outcome. PPT(1).pptx
PPT
MA EdLM Organization Communication Chapter 7 ppt.ppt
PPT
MA EdLM Organization Communication Chapter 7 ppt.ppt
PPTX
“_የንባብ_ሕመምን_በንባብ_ክሊኒክ_ማከምማከምከት ምህርት ብቃትና ንቃት አንፃር ሲታይ _”_2015.pptx
PDF
456bd-classrooms-assessement-techniques.pdf
PPTX
2017 EMIS Training-Experts for principals and cluster supervisory brsides to ...
PPTX
Basic Concepts of Organization and Management.pptx
1a. position papeEDUCATIONr and its concern.pptx
Evidences_for_the_existence_of_the_changes_in_the_new_grade_10_Physics.pptx
table of specification for teachers principals and educational leaders .pptx
2021 Education Sector Aanlysisof secondey and higher education MA.ppt
hool-leadersrevised-drafCommunication and Interpersonal Skillst -presentation...
TEXTBOOK PRINTING AND DISTRIBUTION IN SOUTHERN ETHIOIAPPT edited.pptx
የትምህርት ስብራት ለመጠገን እኔም ድርሻ አለኝ የመማሪያ መፅሀፍት አቅርቦትና የት/ት ጥራት
1 Physiology of Pregnan women Unit1-1.pptx
Ayalueffects of transformational leadership on students outcome. PPT(1).pptx
MA EdLM Organization Communication Chapter 7 ppt.ppt
MA EdLM Organization Communication Chapter 7 ppt.ppt
“_የንባብ_ሕመምን_በንባብ_ክሊኒክ_ማከምማከምከት ምህርት ብቃትና ንቃት አንፃር ሲታይ _”_2015.pptx
456bd-classrooms-assessement-techniques.pdf
2017 EMIS Training-Experts for principals and cluster supervisory brsides to ...
Basic Concepts of Organization and Management.pptx

ትምህርት ምዜ አዘገጃጄት ዜደ ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት ቤቶች.pptx

  • 1. በጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የትም/ምዘና ጥናትና የፈተና ዝግጅት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ለወረዳ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ለትምህርት አመራሮችና ለትም/ቤት መምህራን በፈተና ቢጋር አዘገጃጀት ዙሪያ የተዘጋጀ የገንዛበ ማስጨበጫ ስልጠና ታክሳስ 2017 ዓ.ም አርባምንጭ
  • 2. የስልጠና ሰነድ ዋናዋና ይዘቶች መግቢያ የትምህርት ምዘና ምንነት/ትርጉም የምዘና ዓላማዎች በፈተና ዕቅድና ዝግጅት ወቅት ትኩረት የሚሹ ጉዳዬች 1. የምዘናውን ዓላማ መወሰን 2. የሚለኩትን የመማር ውጤቶች መለየት 3.የትምህርት ውጤቶችን መግለጽ 4.የሚለካውን የትምህርት ይዘት መዘርዘር መሠረታዊ የፈተና ባህርያት የምዘና እቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ማዘጋጀት (TABLE OF SPECIFICATION) የምርጫ ጥያቄ አይነቶች፡ጥንካሬ፣ድክመት፣ የጥያቄና አማራጮች ማዘጋጃ መመሪያዎች
  • 3. መግቢያ • የአንድ ሀገር ሥርዓተ ትምህርት በተፈለገዉ አቅጣጫ እየተከናወነ መሆኑንና አጠቃላይ የትምህርቱ ዓላማ ግብ መምታቱን ለማረጋገጥ ከምንጠቀምባቸዉ ስልቶች አንዱ ፈተና ወይም የትምህርት ምዘና ነዉ። • የትም/ምዘና ዋና ዓላማ በየእርከኑ ወይንም በየደረጃዉ ተመጥኖ የተዘጋጀዉን የሥርዓተ ትምህርት ይዘት በወቅቱ መጠናቀቁን በዚህም ተማሪዎች ተገቢዉን ዕዉቀትና ክህሎት በመጨበጥ የባህርይ ለዉጥ ማምጣታቸዉን ለመለካት የምንጠቀምበት የመማር ማስተማር ሂደት አካል ነዉ። • የክፍል ፈተና በሚዘጋጅበት ወቅት ሥርዓተ ትምህርትን መሠረት በማድረግ በየትምህርት ዓይነቱ በመርሀ-ትምህርት/Syllabus/ ዉስጥ ባሉት ይዘቶች/ምዕራፎች፣ ርዕሶችና ንዑሳን ርዕሶች በዝርዝር ዓላማዎች ላይ ተመሥርቶ ከተማሪዎች የሚጠበቁ የዕዉቀት፣ የክህሎትና የባህርይ ለዉጦችን ልለካ በምችል መልኩ የጥያቄ ስፐሲፊኬሽን ዝግጅት ይካሄዳል።
  • 4. …የቀጠለ በዚሁ መሠረት በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ክፍል መማሪያ መፅሐፍት ይዘት ተለይቶና ተመጥኖ በተዘጋጀዉ ካሪኩለም/ይዘት ስፔሲፊኬሽን እንደ ዝርዝር የዕዉቀት ዘርፉና የክፍለ ጊዜ ድልድሉ መሠረት ምን ያህል ጥያቄ እንደሚወጣ የሚገልጽ መዘርዝር ይዘጋጃል። ከዚህ አንጻር አዘጋጅ መምህራን የፈተና አዘገጃጀት ሥርዓትና መርሆዎችን አዉቀዉ በጥንቃቄ እንዲያዘጋጁ ለማድረግ የትምህርት አመራሩም ሆነ ባለሙያው በአዘገጃጀቱ ዙሪያ የጠራ ግንዛበ አንዲይዝና አውቀው እንዲመራ አቅጣጫ የሚያሳይ የክፍል ፈተና ቢጋር አዘገጃጀት ዙሪያ እየተፈጠሩ ያሉ ክፍተቶችን ለማጥበብ ይህ ስልጠና ሰነድ ተዘጋጅቷል። ሰነዱ በዉስጡ የፈተና ጥያቄ አዘገጃጀት እና የፈተና ጥያቄዎች ዓይነት እንዲሁም ሌሎችንም ቴክኒካል ነጥቦችን አካቶ ይዟል።
  • 5. የስልጠናው ዋና ዓላማ በምዘና ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርጉ የትምህርት አመራራሮችና ባለሙያዎች መምህራን ፈተና ሲያዘጋጁ መሠረታዊ የፈተና ዕቅድ(Table of Specification) አዘገጃጀት ላይ ግንዛቤ ኖሯቸው በስታንዳርዱ መሠረት ጥራቱን የጠበቀ ፈተና እንዲያደርጉ ለማስቻል፡፡
  • 6. የትምህርት ምዘና ማለት ምን ማለት ነዉ? የትምህርት ስርዓትን በተመለከት ውሳኔ ለመስጠት መረጃ የሚሰበሰብበት ሂደት ነዉ፡፡ የተማሪዎችን ውጤት (ተግባር) በጥንቃቄ በተሰበሰበ መረጃ ላይ ተመስርቶ የመመርመር፣ የመተንተንና የመተግበር ሥራ ነው፡፡ ስለ ካሪኩለምና መርሃግብር ፤ስለመምህራን የትምህርት አሰጣጥና የተማሪዎች የትምህርት አቀባበል፤ስለትምህርት ፖሊስ ለመወሰን የሚያስችል መረጃ የመሰብሰብ ሂደት ነዉ፡፡ ምዘና የማያርጥ ሂደት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ማለት በተከታታይ ምዘና፣በሚድ በሴ/ር፤በዓመት ማጠቃላይ ፤በሦስት ዓመት፤በትምህርት እርከን ማጠቃላይ ለምሳሌ በ1ኛ ደረጃ /በሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሊሰጥ ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ተማሪዎች ተገቢዉን ዕዉቀትና ክህሎት መጨበጣቸዉን እንዲሁም መምህራን በአግባቡ ማስተማራቸዉን ለማረጋገጥ የሚደረግ መረጃ መሰብሰቢያ ሂደት ነዉ፡፡
  • 7. የምዘና ዓይነቶች ሂደታዊ ምዘና ;-ተከታታይ ምዘና ሲሆን የማስተማሩን ሥራ ለማሻሻልና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ከመፈለግ የተነሣ የክፍል ውስጥ መልስ ማየትና ምልከታን የማስተማር ሂደት አካል አድርጎ ይቀበላቸዋል፡፡ የማጠቃለያ ምዘና በልዩ ሁኔታ የአንድን የማስተማር ፕሮግራም ዓመታዊ ሥራ ሲጠናቀቅ ውጤታማነትንና አገልግሎቱን የመገምገም ወይም አንድ የማስተማር ደረጃ ሲገባደድ በቅድሚያ በተወሰነ ጊዜ የተማሪ ብቃት ላይ ዳኝነት ለመስጠት መረጃ መሰብሰቢያ ሂደት ነዉ፡፡ ተማሪዎች ምን እንደሚያውቁና መስራት እንደሚችሉ ለማረጋገጥ፣ የትምህርት ግቦች ላይ መድረስ አለመድረሳቸውን ለማሳየት እና አልፎ አልፎ ከሌሎች ጋር በማወዳደር ተማሪዎች የት ላይ እንዳሉ ለማሳየት ያገለግላል (Stiggins, 2002; Black and Wiliam, 1999) ፡፡
  • 8. የምዘና ዓላማዎች ውጤት ለመስጠት የተማሪዎችን የስራ ክንውን በምስክር ወረቀት ለማረጋገጥ ተማሪዎችን ለመምረጥ ተማሪዎችን ለመመደብ ለመምራትና ለማማከር የአስተዳደራዊ የፖሊሲ ውሳኔዎች ለመስጠት የፕሮግራም ምዘና ውሳኔዎች
  • 9. የፈተና ዕቅድ አስፈላጊነት የፈተና ዕቅድ ማለት (It is known as Test blue print) የፈተና ጥያቄዎች ከመዘጋጀታቸዉ በፍት ታሳቢ ሊሆን የሚገቡ ቅድመ ፈተና ዝግጅቶችን ተጨባጭና ግልጽ በሆነ መልክ የሚታቀድ ነዉ፡፡ሆኖም በርካታ መምህራን ምዘናዎችን ያለ ዕቅድ ማዘጋጀታቸዉና መፈተናቸው በተማሪዎች ውጤት እና በትም/ት ፖሊሲ አተገባር ላይ አሉታዊ ተጽኖ አለዉ፡፡ በመሆኑም ምዘናዎችን ከማካሄዳችን በፊት ማቀዳችን የሚከተሉ ጠቀሜታዎች ያስገኛል፡- ተማሪዎች የተማሩትን የትም/ት ይዘት ሽፋን ለይተን እንዲናዉቅ ያግዘናል፤ የትም/ት ይዘቶች ለማስተማር የወሰዱት ክ/ጊዜ ብዛት፤ የትም/ቱን አጠቃላይ እና ዝርዝር ዓላመዎችን መጠንና ዓይነት እንዲናዉቅ ያግዘናል የተማሪዎችን ዕድሜ እና የዕዉቀት ደረጃ ያገናዘቡ ጥያቄዎችን እንዲናወጣ ያግዘናል ይዘቱ ከወሰደዉ ክ/ጊዜ አንጻር ተመጣጣኝ ፣ተገቢ እና ጥራት ያለዉን ፈተና እንዲናወጣ ይረዳናል፡፡ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ካጠናቀቁ በኋላ ማሳየት የሚገባቸዉን የዕዉቀት፣ክህሎት እና የባህር ለዉጦችን ለይተን እዲናዉቅ ይረዳናል
  • 10. የምዘና መሳሪያዎች (ፈተናዎች) ዕቅድና ዝግጅት የፈተና ጥያቄ አዘጋጆችና መምህራን በጽሁፍ ምዘና መሳሪያዎች እቅድ ወቅት ተከታታይነት ያላቸው እርምጃዎችን ይጠቀማሉ፡፡ 1. የምዘናውን ዓላማ መወሰን የምዘና መሳሪያዎችን በመማር ማስተማር መርሃግብር ውስጥ 1/አንድን ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ለመመዘን (የምደባ ምዘና)፣ 2/የመማር መሻሻልን ለመከታተል (ሒደታዊ ምዘና)፣ 3/የመማር ችግርን ለመመርመር (ምርመራ ተኮር ምዘና)ና 4/የተማሪዎችን ችሎታ/ክንዋኔን ትምህርቱ ሲጠናቀቅ ለመለካት (አጠቃላይ ምዘና) እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ የምዘና መሳሪያ ዓይነት ከዓላማው አንፃር እንዲጣጣም ለማድረግ በንድፉ ላይ ጥቂት ማሻሻያ ይፈልጋል፡፡
  • 11. …የቀጠለ 2.የሚለኩትን የመማር ውጤቶች መለየት የመማር ውጤቶች ከአጠቃላይ የትምህርት ዓላማዎች የሚመነጩትንና ተማሪዎች በትምህት መጨረሻ ላይ ይደርሱባቸዋል ተብለው የሚጠበቁ ውጤቶች መግለጫዎች ናቸው፡፡ ሁሉንም የሚያካትት ዝርዝር የትምህርት ዓላማዎች ለማዘጋጀት ጠቃሚው መመሪያ የትምህርት ዓላማዎች ምደባ (Taxonomy of Educational Objectives) ነው፡፡ ይህ የትምህርት ዓላማዎች ምደባ ሁሉንም የሚጠበቁ የትምህርት ውጤቶችን ለመለየትና ለመመደብ ይረዳል፡፡ እነዚህም ዓላማዎች በሚከተሉት ሶስት ዋና ዋና ዘርፎች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡
  • 12. የትምህርት ዓላማዎች ምደባ 2.የዝንባሌ ዘርፍ (Affective Domain) የግንዛቤ ዘርፍ ( Cognitive Domain ) እውቀት(Kn owledge) መረዳት/ መገንዘብ(C omprehensi on መተግበር/ ትግበራ(Ap plication) Analysis, Synthesis, and Evaluation, ) የክህሎት ዘርፍ (Psychomoto r Domain) የቤተ-ሙከራ የተግባር የመግባባት የማስላት የማህበራዊ
  • 13. …የቀጠለ 1. የግንዛቤ ዘርፍ/ ( Cognitive Domain ) ይህ የእውቀት ዘርፍ ቀላል እውቀት (Simple Knowledge) ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ተማሪዎች ለሚጠየቁት ነገር አንድና ቀላል ምላሽ የሚሰጡት ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ከተማሪዎች የሚጠበቅ ዋነኛ ጥረት የተማሩትን ነገር በመሸምደድ ያንኑ ፍሬ ነገር እያስታወሱ ( Memorization) መስራት መሆኑ ታውቆ ይህንን መመዘን የሚያስችሉ ጥያቄዎች ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
  • 14. …የቀጠለ ሀ.እውቀት(Knowledge) አንድን ነገር መረዳት፤መጠቀም ወይም መለወጥ ባይቻልም ማስታወስ መቻል ስያሜዎች  ዝርዝር እውነታዎች ጽንሰ ሃሳቦችና መርሆዎች ለ. መረዳት/መገንዘብ(Comprehension)፤-አንድን ነገር ከሌላ ከምንም ነገር ጋር ሳይዛመድ(ሳይነፃፀር) የተላለፈዉን መልዕክት መገንዘብ ጽንሰ ሃሳቦችና መርሆዎች ዘዴዎችና የአሰራር ሂደቶች የጽሁፍ ማቴሪያሎች፣ግራፎች፣ካርታዎችና በቁጥር የተገለፀ መረጃ የችግር ሁኔታዎች ሐ. መተግበር/ትግበራ(Application)፡-አስፈላጊ በሆነበት ሁኔታ አጠቃላይ ግንዛቤን በመጠቀም ችግሮችን መፍታት፤የተማሩትን ነገር በአድስና ተጨባጭ ሁነታ ላይ መጠቀም፤ ተጨባጭ መረጃ ጽንሰ ሃሳቦችና መርሆዎች ዘዴዎችና የሥራ ሂደቶች ችግር የመፍታት ክህሎት
  • 15. ….የቀጠለ  ከፍተኛ የአስተሳሰብ ደረጃ የሚጠይቁ ክህሎቶች(መተንተን፣ ማቀናበርና መገምገም) (Analysis, Synthesis, and Evaluation,)  በጥልቀት ማሰብ ችግር መፍታት   አስተሳሰብ  አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር  2.የዝንባሌ ዘርፍ (Affective Domain) ይህ ዓላማ የተማሪዎች ዝንባሌ፣ ፍላጎት፣ ምኞች፣ ምርጫ፣ ወዘተ መቀየር ማስቻሉን ወይም ደግሞ ተማሪዎች ያመኑበትን፣ የወደዱትን ነገር፣ ዋጋ የሰጡትን ጉዳይ ሳያወላውሉና ሳያቋርጡ በስራ ላይ ማዋላቸውን የሚያመላክት ሲሆን መምህራን በዚህ መልክ ተረድተው በምዘና ወቅት ተግባር ላይ ማዋል አለባቸው፡፡
  • 16. ….የቀጠለ ሀ. ዝንባሌዎች(Attitudes )  ማህበራዊ ዝንባሌዎች ሣይንሳዊ ዝንባሌዎች  ለ. ፍላጎቶች(Interests ) የግል ፍላጎቶች  ትምህርታዊ ፍላጎቶች የሙያ ፍላጎት ሐ. አድናቆቶች(Appreciations )  ስነጽሁፍ፣ ጥበብና ሙዚቃ  ማህበራዊና ሳይንሳዊ ስኬቶች መ. ማስተካከሎች(Adjustments )  ማህበራዊ ማስተካከሎች  ስሜታዊ ማስተካከሎች
  • 17. ….የቀጠለ 3. የክህሎት ዘርፍ (Psychomotor Domain) ይህ ዓላማ ተማሪዎች በአእምሮአቸው የያዙትን ነገር የአካል ክፍሎችን በመጠቀም ችሎታቸውን (skills) በስራ ላይ ማዋልን ይመለከታል፡፡ ተማሪዎች እጅና አእምሮን በማቀናጀት በተግባር ሰርተው የሚያሳዩት ነገር በክህሎት ዘርፍ በመጠቀም እንደሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ የቤተ-ሙከራ ክህሎት የተግባር ክህሎት የመግባባት ክህሎት የማስላት ክህሎት የማህበራዊ ክህሎት
  • 18. Some list of Action Verbs in Learning Outcomes
  • 19. 3. የትምህርት ውጤቶችን መግለጽ የመማር ውጤቶችን የመጠቀም ዋነኛው ምክንያት ተማሪው/ዋ ሊያሳይ/ልታሳይ የሚገባውን የመማር ብቃቶች በመለየት የተወሰነውን ክህሎት ወይም የተቀመጠውን እውቀት ማወቅ አለማወቁን/ቋን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ጠቃሚ የትምህርት ውጤቶች የሚመነጩት ከእውቀት ዘርፍ (የአእምሮ ክህሎቶች፣ እውቀት ወይም አስተሳሰብ)፣ ስሜታዊ ዘርፍ (በኃይለ-ስሜት መጎልበት፣ አመለካከት)ና ከክህሎት ዘርፍ (የአንድ ነገር አሰራር መመሪያ፣ አካላዊ ክህሎት/ድርጊቶች) ነዉ፡፡ እነዚህ ዓላማዎች ዝርዝር፣ የሚለኩ፣ ተጨባጭ፣ ጠቃሚና ውጤት ተኮርና በተወሰነ የጊዜ ገደብ የሚተገበሩ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  • 20. 4. የሚለካውን የትምህርት ይዘት መዘርዘር የትምህርት ውጤቶች ተማሪዎች የትምህርቱን ይዘቶች እንዴት ሊተገብሩ እንደሚችሉ የሚወስኑ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የተማሪዎችን ባህሪና ዝርዝር የትምህርት ይዘትን በተመሳሳይ ዓረፍተ ነገር መግለጽ ቢቻልም፣ ብዙ ጊዜ ለየብቻቸው መዘርዘር አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ተማሪው/ዋ ለብዙ የተለያዩ የትምህርቱ ይዘት ክፍሎች በተመሳሳይ መንገድ ምላሽ ሊሰጥ/ልትሰጥ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ተማሪው/ዋ በበርካታ የተለያዩ መንገዶች ለአንድ የይዘት ክፍል ምላሽ ሊሰጥ/ልትሰጥ ይችላል/ትችላለች፡፡ ለምሣሌ፡- ተማሪው/ዋ፡- “ ” “ ስያሜን በራሱ አባባል ይገልፃል ፣ ውስን እውነታዎችን ” “ ” ያስታውሳል ወይም የመርህ ምሳሌ ይሰጣል ብለን ብንገልጽ፤ እነዚህ ባህሪያት በየትኛውም የትምህርቱ ይዘት ክፍል ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ፡፡
  • 21. መሠረታዊ የፈተና ባህርያት  ፈተና ሲዘጋጅ አምስቱ የፈተና ባህርያት በጥንቃቄ መታየት አለባቸዉ። እነዚህም፦ 1/ የፈተና አስተማማኝነት /Reliability/፦ ከተማሪዎቹ ዕድሜና የክፍል ደረጃቸዉ አንጻር እና የትም/ዓላማዉን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ምዛናዊ የሆነ አስተማማኝ ፈተና 2/ የፈተና ተጨባጭነት/Objectivity/፦ግልጽ የሆኑና ተማሪዎች በተማሩት ይዘቶች ላይ የተመሠረቱ ጥያቄዎችን ያካተተ፣
  • 22. ………..የቀጠለ 3/ የሚዘጋጀዉ ፈተና ጎበዙን ተማሪ ከደካማው መለየት የሚችል /A test with discriminating Power/ 4/ የፈተናዉ ተመጣጣኝነት / Level of Difficulty /፦ በጣም ያልከበደና በጣምም ያልቀለለ ለደረጃዉ የሚመጥን ፈተና፣ 5/ ከተማሪው የሚፈለገዉን የዕዉቀት ደረጃ የመለካት ብቃት /Validity/ያለው፦ ለደረጃዉ የተቀመጠዉን ፕሮፋይል የሚያሟላ ፈተና መዘጋጀት እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል በዚህ መሠረት የማጠቃለያም ሆነ የክፍል ፈተና ጥያቄዎች ሲዘጋጁ 6 ዋና ዋና የዕውቀት ዘርፎችንና/cognitive domains/ በዕውቀት ዘርፍ ሥር ያሉትን ንዑሳን ዘርፎችን ማለትም
  • 23. በስፔሲፊኬሽን የጥያቄዎቹን ብዛት፣ ከክፍለ ጊዜ ፣ ከክብደትና ቅለት አንጻር መዋቀሩን እርግጠኛ መሆን፣ ይህም ማለት በ Bloom’s Taxonomy of Behavioral Dimention መሰረት መሰራቱን ማረጋገጥ እነሱም፡ -እውቀት /Knowledge/ - አንብቦ መረዳት/መገንዘብ /Comprehension/ -ትግበራ /Application/ - ትንተና/ Analysis/ - ማዋቀር /Synthesis/ -ግምገማ/ Evaluation /ናቸው ለዞናዊ ፈተና በወጥነት የሚዘጋጅ ሞዴል ፈተናም ሆነ ለማንኛውም የክፍል ፈተና አዘገጃጀት ተማሪዎች በዝቅተኛው የትምህርት ቅበላ መሟላት ከሚጠበቅባቸው ፕሮፋይል አንፃር የሚታይ መሆን አለበት፡፡
  • 24. ………….የቀጠለ በመሆኑም የፈተና አዘገጃጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመጣው ከተፈታኞች ብዛት አንጻር እርማት እንዲያመችና የተማሪዎችን ውጤት በወቅቱ በመግለጽ ትምህርት ለማስጀመር እንዲቻል የፈተና አዘገጃጀቱ ሁሉንም የፈተና ዓይነቶችን ከማካተት ይልቅ አማራጮችን ያካተቱ ጥያቄዎችን ( Multiple choice Questions) ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጎ ተግባራዊ እየሆነ ቆይቷል፡፡
  • 25. የምዘና እቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ማዘጋጀት (TABLE OF SPECIFICATION) የምዘና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ የፈተና ዕቅድ በመባል ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ የምዘና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ዓላማዎች የምዘናን ጥያቄዎች ከሚከተሉት ጉዳዮች ጋር ማቀናጀት ነው፡፡ እነሱም፡ ማንኛውንም የይዘት ክፍል ለማስተማር የሚወስደው ጊዜ፣ በተማሩት የትምህርት ዓይነት የመማር ብቃት፣ በብቃቶቹ ወይም በተቀመጡት መስፈርቶች የሚፈለገው የአስተሳሰብ ደረጃ፣ በምዘና ውስጥ ምን እንደተካተተና ይዘቱም ከተቀመጡት መስፈርቶች ጋር መዛመዱን ማወቅና የምዘናውን ጥያቄዎች ጥራት መጨመር ናቸው፡፡
  • 26. …የቀጠለ በመቀጠል ተማሪዎቹ ለእያንዳንዱ የይዘት ክፍል ምን ምን የባህሪ ለውጥ እንደሚያሳኩባቸው በዕውቀት ዘርፍ ደረጃዎች መወሰን፡፡ ለምሳሌ ምን ያህል ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማቴሪያሉን ተረድተውታል? ተማሪዎች በሂደት ውስጥ ያለውን ተገቢ ተግባር መለየት (እውቀት)፤ ጽንሰ-ሃሳቦችን በራሳቸው አባባል ማብራራት(መረዳት)፤ መርህን ወይም ሂደትን በአዲስ ሁኔታ ውስጥ ስራ ላይ ማዋል (መተግበር) የእቅድ ዝርዝር ክፍሎችን ማወዳደርና ማነፃፀር (ትንተና)፤ ወይም ችግርን ለመፍታት እቅድ ማቀድ (ማቀነባበር)ይችላሉን? የፈተናውን ጥያቄ ብዛት መሠረት በማድረግ ከየይዘቱ የሚወጡ ጥያቄዎችን ለማስተማር ከወሰደው ክፍለ ጊዜ አንፃር በመቶኛ ማስላት ያስፈልጋል
  • 27. …የቀጠለ የጥያቄ ብዛት መወሰን የሚያስችል ቀመር የጥያቄ ብዛት= የክፍለ ጊዜ ብዛት x ጠቅላላ የጥያቄ ብዛት አጠቃላይ ክፍለ ጊዜ ብዛት የፈተና ጥያቄዎች ብዛት ሲወሰን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ሁሉም ተማሪዎች ፈተናውን እንዲጨርሱ በቂ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት ነው፡፡ ጥያቄው ከቀላል የማስታወስ ችሎታ በላይ የሚለካ ከሆነ ቢያንስ አንድ ደቂቃ መስጠት ይገባል፡፡
  • 28. …የቀጠለ የፈተና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ዝግጅት አሰራር ቅደም ተከተል በሚቀጥሉት ሁለት እንደ አርአያ በተወሰዱ ምሳሌዎች በሁለት ሠንጠረዥ ቀርበዋል፡፡ የፈተና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ምሳሌ የትምህርት ቤቱ / የተቋሙ ስም፡- --------- የትምህርት ዓይነት፡- --------- የክፍል ደረጃ፡- ------------ የፈተናው ዓላማ፤- ሀ) ተማሪዎቹ በትምህርት ያመጡትን የባህሪ ለውጥ ለመመዘን ለ) በትምህርቱ ተማሪዎች ያሳዩትን የመማር መሻሻል ለመከታተል ሐ) በትምህርቱ የገጠማቸው የመማር ችግር ካለ ለመለየት መ) በመማር-ማስተማር ስልቶች ላይ ግብረ መልስ ለማግኘት
  • 29. የጥያቄዎችን መጠን አወሳሰን የሚያሳይ የፈተና ዕቅድ ሠንጠረዥ 1/T/S/FOR DETERMINING THE PROPORTION ITEMS Major and Specific Content areas (ዓበይና ንዑስ ይዘቶች(ርዕሶች) Period Allotmen t Number of questions in relation to period allotment Number of Questions (%) Formula for deciding the No of questions Number of periods X total items Total number of periods 1. Rational numbers 32 30 100% 1.1 The concept of Rational 9 8 28.1% Eg. 9 X 30 = 8.45 = 8 32 1.2 The order of Rational numbers 7 7 21.8% Eg. 7 X 30 = 6.56 = 7 32 1.3 Operation of rational numbers 1.3.1 Addition Rational numbers 4 4 13% Eg. 4 X 30 = 4 32 1.3.2 Subtraction of Rational numbers 3 3 10% Eg. 3 X 30 = 3 32 1.3.3 Multiplication of Rational numbers 6 5 17% Eg. 6 X 30 = 5 32 1.3.4 Division of Rational numbers 3 3 10% Eg. 3 X 30 = 3 32
  • 30. የትምህርት ዓላማ መሠረት ያደረገ የፈተና ዕቅድ መመሪያ
  • 31. ሠንጠረዥ 3 .የጥያቄ ዓይነትን መሠረት ያደረገ የፈተና ቢጋር
  • 32. ------- --የቀጠለ የትምህርት ዘመን ----------------------------------  የአዘጋጅ መ/ር ስም ------------------- ---ፊርማ ----------- ቀን ----------  የድፓርቲ መንት ኃላፊ ስም---------------ፊርማ ------------- ቀን ------ የር/መ/ር ስም ----------------------- ፊርማ ----------- ቀን -------- ማሳሰቢያ ፡ - ይህ የፈተና ቢጋር የተዘጋጀው በ7ኛ ክፍል ሒሳብ በአንድ ምዕራፍ ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀ ሲሆን መምህራን የፈተና ቢጋር ማዘጋጀት ያለባቸው አስተምረው በሸፈኑት ምዕራፍ ላይ መሆን አለበት ፡፡
  • 33. …የቀጠለ በመቀጠል የጥያቄ ዓይነቶች ላይ መወሰነ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በትምህርቱ ዓላማዎችና በሚለካው ይዘት ባህሪ ይወሰናል፡፡ በሠንጠረዥ ላይ የተገለፀው የፈተና ዕቅድ መመሪያ ሠንጠረዥ ከይዘቱ ጋር የሚሄዱትን ተገቢ የጥያቄ አይነቶችን ለመወሰንም ይረዳናል፡፡ እዉነት /ሐሰት አዛምድ ባዶ ቦታ ሙላ ምርጫ አብራራ
  • 34. የምርጫ ጥያቄ የምርጫ ፈተና ጥያቄዎችን ማዘጋጀት የምርጫ ፈተና/ጥያቄ ምላሽ የሚፈልግ ችግርንና አማራጭ መልሶችን አካቶ ይይዛል፡፡ ምላሽ የሚፈልገው ችግር በቀጥታ ጥያቄ ወይም ባልተሟላ ዓረፍተ ነገር መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ምላሽ የሚፈልገው ችግር የጥያቄው ግንድ ሲባል እንደመፍትሔ ጥቆማ በዝርዝር የተቀመጡት ደግሞ አማራጭ መልሶች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከቀረቡት አማራጭ መልሶች ውስጥ አንዱ ትክክለኛ መልስ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ አሣሣች መልሶች በመባል ይታወቃሉ፡፡ አማራጭ መልሶቹ ቃላትን፣ ምልክቶችን፣ ቁጥሮችን፣ ሐረጎችን ወዘተ ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡
  • 35. የምርጫ ጥያቄ አይነቶች፡ i. ዝግ ግንድ ጥያቄ (Closed stem)፡- ዝግ ግንድ ምላሸ የሚያስፈልገውን ጥያቄ የሚያቀርብ ነው፡፡ ዓረፍተ ነገሩ የሚጠናቀቀው በጥያቄ ምልክት ነው፡፡ ምን እንደተጠየቀ ግልጽ በሆነ መንገድ ያስቀምጣል፡፡ አንባቢዎችን/ተፈታኞችን ወደ አማራጭ መልሶች ይመራቸዋል፡፡ አማራጭ መልሶቹ ስዕሎች፣ ዲያግራሞች፣ ሠንጠረዦች በሚሆኑበት ጊዜ የጥያቄው ግንድ ዝግ መሆን አለበት፡፡ ምሣሌ፡- ከሚከተሉት ውስጥ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የቱ ነው?
  • 36. …የቀጠለ ii. ያልተገደበ ክፍት ግንድ ጥያቄ (Open stem)፡- ያልተሟላው ዓረፍተ ነገር ከአማራጮቹ በአንዱ ይሟላል፡፡ አጠር ያለና ቀጥተኛ፤ ያልተገደበ ነው፡፡ አማራጭ መልሶቹ ከጥያቄው ግንድ ጋር በሰዋሰው ስርዓት ተስማሚ መሆን አለባቸው፡፡ ምሣሌ፡- የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ------------- ነው፡፡
  • 37. …የቀጠለ ጠንካራ ጎኖች የትምህርቱን ይዘት በስፋት መወከል ያስችላል፡፡ እርማቱ ቀላልና ተጨባጭ ነው፡፡ የጥያቄ ትንተናን ለማከናወን ይጠቅማል፡፡ የተማሪዎችን ችግር ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል፡፡ በሁሉም የትምህርት እርከኖች ላይ መጠቀም ይቻላል፡፡
  • 38. ደካማ ጎኖች oየመማር ውጤቶችን በቃል (በሐረግ) ደረጃ መለካት ላይ የተወሰነ/የተገደበ ነው፡፡ oሃሳብን የማደራጀትና የማቅረብ ችሎታን አይለካም፡፡ o መልስ የሚመስል አሳሳች መልስ ማዘጋጀት/ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡
  • 39. የምርጫ ጥያቄዎች ለማዘጋጀት የሚረዱ መመሪያዎች  እያንዳንዱ ጥያቄ ውስን ይዘትና አንድ ውስን የመማር ውጤትን/ዓላማን ማንጸባረቅ አለበት፣  እያንዳንዱን ጥያቄ ለመማር ጠቃሚ በሆነ ይዘት ላይ እንዲመሠረት ማድረግ፤ የማይረባ ይዘትን ማስወገድ ያስፈልጋል፣  ከፍተኛ የመማር ደረጃን (higher level learning) ለመፈተን አዳዲስ ነገሮችን መጠቀም ያስፈልጋል፣ የመማሪያ መጽሐፍ ቋንቋን ወይም በመማር ማስተማር ወቅት እንጠቀምበት የነበረን የቋንቋ አጠቃቀም በቀጥታ እንዳለ ከመውሰድ ይልቅ ለወጥ ባለ መልክ በመጠቀም ጥያቄው ከቀላል የማስታወስ ብቃት የተሻለ እንዲለካ ማድረግ፣ የእያንዳንዱን ጥያቄ ይዘት በሌላ ፈተና ጥያቄዎች ይዘት ላይ እንዳይመሠረት ጥንቃቄ ማድረግ፣
  • 40. …የቀጠለ የምርጫ ጥያቄ ሲዘጋጅ በጣም ውስንና በጣም አጠቃላይ ይዘትን ማስወገድ፣ አስተያየት ላይ የተመሠረቱ ጥያቄዎችን ማስወገድ፣  ጥያቄዎች ሲዘጋጁ ጥቅም ላይ የሚውሉት ቃላት በተቻለ መጠን ለተፈታኝ ተማሪዎች ቀላል እንዲሆኑ ማድረግ፣ ጥያቄዎቹ ከግድፈት የፀዱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እርማት ማከናወን ተገቢ ነው፣  ትክክለኛ ሰዋሰው፣ ሥርዓተ ነጥብና የፊደላት አጻጻፍ (ሥርዓተ ሆሄያት) መጠቀምና የእያንዳንዱን ጥያቄ ማንበቢያ ጊዜ ለመቀነስ በጣም ረጅም የሆኑ ጥያቄዎችን ማስወገድ፡፡
  • 41. የጥያቄ ግንዶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ መመሪያዎች የጥያቄ ማዘጋጀት ግቡ ተማሪዎች ምን እንደሚያውቁና ማከናወን እንደሚችሉ ለመረዳት እንጂ የሚሸውዱ ጥያቄዎችን ለማዘጋጀት አይደለም፡፡ የምርጫ ጥያቄ ግንዱን ስናዘጋጅ ልንከተላቸው የሚገቡ ጥቂት መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የጥያቄውን ግንድ በጥያቄ መልክ ወይም ባልተሟላ ዓረፍተ ነገር መልክ መግለጽ  የጥያቄ ግንድ ለመጻፍ ያልተሟላ ዓረፍተ ነገር የምንጠቀም ከሆነ የሚሞላውን ባዶ ቦታ የዓረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ወይም መሀል ላይ አለማድረግ፣ የጥያቄው ግንድ ውስጥ ያለው ትእዛዝ ግልጽና የቃላት አጠቃቀሙም ተፈታኞቹን ምን እንደተጠየቁ የሚያሳውቋቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣  እያንዳንዱ ጥያቄ ዝርዝር የመማር ውጤትን እንዲለካ ማድረግ፣ በጥያቄው ግንድ ውስጥ ከሚፈለገው በላይ ቃላትን ማጨቅ ማስወገድ፣ የጥያቄውን ግንድ በተቻለ መጠን በአወንታዊ አባባል መግለጽ፣ አሉታዊ አገላለጽን ማስወገድ
  • 42. …የቀጠለ ዋናውን ሃሳብ በጥያቄው ግንድ ውስጥ ማካተት፣ የጥያቄው ግንድ በተገቢው አገላለጽ ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ መግለጽ አለበት፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ በዓረፍተ ነገር ውስጥ ሁልጊዜም ግስ እንዲካተት ማድረግ፣ ከፍተኛ የአስተሳሰብ ደረጃን ለመለካት የምርጫ ጥያቄን መጠቀም ይቻላል፣  የምርጫ ጥያቄዎች ራሳቸውን ችለው መቀረጽ አለባቸው፡፡ ይህ ማለት የአንዱ ጥያቄ መልስ በሌላው ጥያቄ መልስ ላይ መመስረት የለበትም፣ የተማሪዎችን የመረዳት፣ የመተግበር፣ የመተንተን፣ የመገምገምና የማስታወስ ችሎታዎችን የሚለኩ ጥያቄዎች ማዘጋጀት ላይ ማተኮር፣ በጥያቄው ግንድ ውስጥ መካተት የሚገባቸውን ሁሉ ማካተት፡፡ በአማራጭ መልሶች ውስጥ ተመሳሳይ አባባሎችን አለመደጋገም፡፡ ይህ የሚቆጥበው ጥያቄውን የመፃፊያ ጊዜ ብቻ ሳይሆን የተማሪዎችንም የማንበቢያ ጊዜ ነውStem: Example In objective testing, the term objective: A. refers to the method of identifying the learning outcomes. B. refers to the method of selecting the test content. C.refers to the method of presenting the problem. D. refers to the method of scoring the answers.
  • 43.  በሚከተለው መልክ የሚጀምርና የማይገናኙ የአማራጮች ስብስብን የሚያስከትል ጥያቄ አለመጠየቅ፡፡ ይኸውም፡- “ከሚከተሉት ውስጥ እውነት/ሐሰት የሆነው የቱ ነው?” ስለዚህ በሚከተለው መልክ “ የሚጀምርና ሁሉም አማራጭ መልሶች አንድ ጉዳይ ላይ X” የሚያተኩር ጥያቄ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ “ “ ከሚከተሉት ውስጥ X”ን በተመለከተ እውነት/ሐሰት የሆነው የቱ ነው?”  የተሟሉ ዓረፍተ ነገሮች ላይ ትክክለኛ ስርዓተ ነጥብ መጠቀም  በአሉታዊ መንገድ የተገለፀ የጥያቄ ግንድ ግራ መጋባትን (መወናበድን) ይፈጥራል፤ ስለዚህ መጠቀም አይገባም፡፡ በአሉታዊ መንገድ የተገለፀን የጥያቄ ግንድ መጠቀም የግድ ከሆነና አሉታዊ ቃሉም አንድ ከሆነ፤ ትኩረት እንዲስብ ቃሉ ሲፃፍ ጎላ የሚልበትን ስልት መጠቀም (ለምሳሌ፡ ከስሩ በማስመር ሊሆን ይችላል)፣
  • 44. ……የቀጠለ በጥያቄው ግንድ ውስጥ የምንጠቀማቸው ቃላት ከተፈታኞቹ የግንዛቤ ደረጃ ጋር የሚመጣጠኑ መሆን አለባቸው፣ የጥያቄው ግንድ ሲዘጋጅ በጣም ውስን እውቀት ላይ ማተኮርን ማስወገድ፣ የጥያቄው ግንድ ሲዘጋጅ በቀጥታ ከተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ ላይ መገልበጥንና አላስፈላጊ ቃላትን መጠቀምን ማስወገድ፣  ተገቢውን ሰዋሰው፣ ስርዓተ ነጥብና የፊደላት አፃፃፍ ስርዓት በወጥነት መጠቀምና  የሚያሳስቱ ጥያቄዎችን ማለትም ተፈታኞች እንዲታለሉና እንዲሸወዱ በማድረግ የተሳሳተ ምላሽ እንዲሰጡ የሚያደርጉ ጥያቄዎችን ማስወገድ
  • 45. አማራጭ መልሶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ መመሪያዎች  አማራጭ መልሶች ተቀራራቢ ርዝማኔ ያላቸውና የአፃፃፍ ዘይቤያቸውም ከትክክለኛው መልስ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ ትክክለኛው መልስ በርዝማኔው፣ በቃላቶች አጠቃቀምና በሌሎች አላስፈላጊ ነገሮች ከአሳሳች መልሶች የተለየ መሆን የለበትም፡፡  በአጠቃላይ በፈተናው ውስጥ ትክክለኛው መልስ በሁሉም የመልስ አማራጮች መካከል መሰራጨት አለበት “ ፡፡ ይህም ማለት ” “ ” “ ” “ ሀ ፣ ለ ፣ ሐ ፣ ና መ” እንደ ትክክለኛ መልስ ተቀራራቢ ድርሻ እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡  አንድ ብቻ ትክክለኛ/በጣም የተሻለ መልስ መኖሩን እርግጠኛ መሆን፣  አማራጭ መልሶች ለሌላ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ፍንጭ መስጠት የለባቸውም፣  ማዘጋጀት የሚቻለውን ያህል ውጤታማ አማራጭ መልሶችን ማካተት ቢቻልም ጥናቶች የሚመክሩት ከሦስት እስከ አረት አማራጭ መልሶችን መጠቀም፡፡  እያንዳንዱ ጥያቄ አንድ ትክክለኛ መልስና ሶስት አሳሳች መልሶች ሊኖሩት ይገባል (ባለአራት አማራጮችን የምንጠቀም ከሆነ )፣ አማራጭ መልሶች በግልጽነት ጉድለትና አሻሚነት የተነሣ ሊያሳስቱ ወይም ሊያደናግሩ አይገባም፣
  • 46. …የቀጠለ አማራጭ መልሶች አንድ አይነት ትርጉም ሊኖራቸው አይገባም፡፡ አሳሳች መልሶቹ አንዱ ከሌላው የተለየ ትርጓሜ ሊኖረው ይገባል፡፡ አሳሳች መልሶች አንድ አይነት መሆን የለባቸውም፡፡ አንድ ውስን ትርጉም ያለው አሳሳች መልስ በሌላ አጠቃላይ ትርጉም ባለው አሳሳች መልስ ውስጥ መካተት የለበትም፣ “ ” ሁሉም መልስ ናቸው “ ” የሚለውን አማራጭ መልስ መጠቀም ማስወገድ፡፡ ሁሉም መልስ ናቸው የሚለው አማራጭ መልስ የሚፈጥረው ችግር ጥያቄውን በጣም ቀላል ማድረጉ ነው፡፡ ተማሪዎች “ ከቀረቡት አማራጭ መልሶች መካከል ቢያንስ አንዱ የተሳሳተ ምላሽ መሆኑን ካወቁ ሁሉም መልስ ” ናቸው የሚለው ምላሽ ትክክለኛ መልስ እንደዳልሆነ በግልጽ ያውቁታል፡፡ በሌላ በኩል ከቀረቡት “ ” አማራጭ ምላሾች ውስጥ ሁለቱ ትክክል መሆናቸውን ካወቁ፣ ሁሉም መልስ ናቸው የሚለው ምላሽ ትክክለኛ መልስ መሆኑን በቀላሉ ያውቁታል፡፡ ተማሪዎች ይህንን ፍንጭ በመጠቀም ፈጣን ምላሸ ይሰጣሉ፣  “ ” ሁሉም መልስ አይደሉም የሚለውን እንደ አማራጭ መልስ መጠቀምን ማስወገድ፡፡ ይህን አማራጭ መጠቀም የሚቻለው ፍጹም/ሙሉ በሙሉ ትክክለኛነትን መለካት በሚቻልበት ሁኔታ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ እንደ ሂሣብ፣ ሰዋሰው፣ ስርዓተ ሆሄያት፣ ጂኦግራፊ፣ ታሪካዊ ቀናት፣ ወዘተ፡፡
  • 47. …የቀጠለ ያለበለዚያ ተማሪዎች ከአማራጭ መልሶቹ ውሰጥ አንዱን አማራጭ መልስ ትክክል ነው እያሉ ሊከራከሩ ይችላሉ፣  ሁለት ወይም ሶስት አማራጮችን በአንድ አማራጭ የሚያካትት አማራጭ መልሶችን መጠቀም ማስወገድ (ምሳሌ፡- ሀ ና መ፣ ሀ ና ሐ፣ ሀ፣ ለ ና ሐ፣ ወዘተ)፡፡  አማራጭ መልሶች በከፊል ትክክል የሆኑ አሳሳች መልሶችን አያካትቱም፡፡ (ለምሣሌ፡- ጥንድ አማራጭ መልሶች ማለት አንደኛው አማራጭ መልስ ትክክለኛ መልስና ሌላኛው አማራጭ መልስ ትክክለኛ መልስ ያልሆነ)፣  ፍፁም መለያዎችን (Absolute qualifiers) ማስወገድ፡፡ ለምሳሌ፡- “ ” “ ” ሁሉም ፣ ሁል ጊዜ ፣ “ ” ፈጽሞ የመሳሰሉት ፍፁም መለያዎች ብዙ ጊዜ ትክክል ባልሆነ አማራጭ መልስ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ አንፃራዊ መለያዎችን (specific qualifiers) መጠቀምንም ማስወገድ ይገባል፡፡ ለምሳሌ፡- “ብዙ ” “ ” “ ” ጊዜ ፣ በተደጋጋሚ ፣ አንዳንድ ጊዜ የመሳሰሉት ግልጽ ያልሆኑ ቃላትን አለመጠቀም፣ ከተቻለ አማራጭ መልሶችን ከጥያቄ ግንዱ ስር አግድም ከመደርደር ወደታች በረድፍ እንዲደረደሩ ማድረግ ይመረጣል፣
  • 48. ምን ያህል ቀላል፣ አማካይና ከባድ ጥያቄዎች እንደሚወጡ
  • 49. በጥያቄዎቹ ላይ ሁከት ተሚፈጥሩና ተቀባይነት የሌላቸዉ ስለ ብሄር ሀይማኖት ጾታ ፖለቲካ አካል ጉዳተኛነትን የሚያንኳስሱ ቃላቶች አለመጠቀም
  • 50. የፈተና ወረቀት ገጽ ሽፋን በፈተና ወረቀቱ የፊትለፊት ሽፋን ላይ ፈተናውን የሚያስተዳድረው ባለቤት ሙሉ ስም፣ ፈተናው አይነት ፣ የጥያቄዎች ብዛት (Number of Items) እና ለፈተናው የተሰጠው ጊዜ (Time Allowed) የመጀመሪያ ፊደላት ከ”of” በስተቀር ሌሎቹ በትልቅ ፊደላት (capital letters) ይፃፋሉ፡፡ በተጨማሪም “hours” በሙሉ በትንሽ ፊደላት (small letters) ይፃፋል፡፡ እንዲሁም የተሰጠው የፈተና ጊዜ በደቂቃ (Minutes) ሳይሆን በሰዓት (hours) መፃፍ አለበት፣ ለምሣሌ 2:00 hours
  • 51. የጥያቄዎችን አፃፃፍ (Items writing) ፡- የፅሁፍ ፊደል መጠን (font size) -­ ­14 የፅሑፍ ፊደል ዓይነት (font type) - በእንግሊዝኛ ለሚፃፉ ፈተናዎች Times New Roman በየፅሑፍቹ መስመሮች መካከል የሚኖረው የቦታ ስፋት አንድ መስመር (single line space) ይሆናል። በጥያቄ ቁጥርና በጥያቄው መካከል ያለው ርቀት -­ ­1.5 በጥያቄ ግንድና በአማራጮቹ መካከል ያለው ርቀት -­ ­1.5 የምርጫ ፊደላት ሲፃፉ በትልቅ ፊደላት (capital letters) ተፅፈው ነጥብ ይደረግባቸዋል፡፡ ምንባብ፣ ለእንግሊዝኛ፣አፍ መፍቻ ቋንቋና አማርኛ እያንዳንዱ አንቀፅ አጠር ያለ ሆኖ ከ150 እስከ 200 ቃላት የያዘ መሆን አለበት