1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ትራምፕ በናይጄሪያ ሁለተኛው የአይ ኤስ አዛዥ መገደሉን ተናገሩ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 8 2018

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የእስላማዊ መንግሥት" ከፍተኛ አባል የነበሩት አቡ-ቢላል አል-ሚኑኪ መገደላቸውን ተናግረዋል። ትራምፕ እንዳሉት አቡ-ቢላል አል-ሚኑኪ የተገደለው በናይጄሪያ ሲሆን የአሜሪካ እና የናይጄሪያ ኃይሎች ባሳተፉበት የጋራ ተልዕኮ ነው።

https://p.dw.com/p/5DpuC
ዶናልድ ትራምፕ፤የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
ዶናልድ ትራምፕ፤የአሜሪካ ፕሬዝዳንትምስል፦ Mark Schiefelbein/AP Photo/picture alliance

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የእስላማዊ መንግሥት" ከፍተኛ አባል የነበሩት አቡ-ቢላል አል-ሚኑኪ መገደላቸውን ተናግረዋል። ትራምፕ እንዳሉት አቡ-ቢላል አል-ሚኑኪ የተገደለው በናይጄሪያ ሲሆን የአሜሪካ እና የናይጄሪያ ኃይሎች ባሳተፉበት የጋራ ተልዕኮ ነው። ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት በትሩዝ ሶሻል በተባለው የመገናኛ ዘዲያቸው  ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ አል-ሚኑኪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጄው  በ"እስላማዊ መንግሥት" (IS) የሽብር ድርጅት ውስጥ ሁለተኛው አዛዥ ነበር።

«ከእንግዲህ ስጋት አይሆንም»

«ከእንግዲህ የአፍሪካን ህዝብ አያስፈራራም ወይም አሜሪካውያንን ኢላማ ለማድረግ የሚያግዝ ዕቅድ አያወጣም» ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአልሚኑኪ መወገድ የአይኤስን ዓለም አቀፍ ዘመቻ "በእጅጉ ይቀንሳል" ብለዋል።ትራምፕ አልሚኑኪን ለመግደል በተልዕኮው ላይ ላበረከተው አጋርነት የናይጄሪያን መንግስት አመስግነዋል።

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቢ በበኩላቸው የአሜሪካ እና የናይጄሪያ የጋራ ዘመቻ «በሽብርተኝነት ትግል ውስጥ ውጤታማ ትብብርን የሚያሳይ ጉልህ ምሳሌ» መሆኑን ተናግረዋል።ቲኑቢ በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ በቻድ ሐይቅ ተፋሰስ በሚገኘው የአልሚኑኪ ግቢ ላይ የተፈፀመው ጥቃት "በርካታ" የእሱን ተከታዮች ጭምር  እንደገደለ አክለዋል።

ቦላ አህመድ ቲኒቡ፤ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት
ቦላ አህመድ ቲኒቡ፤ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትምስል፦ Toyin Adedokun/AFP

በናይጄሪያ  በታጣቂ ቡድኖች የሚፈጸሙ ጥቃቶች

ናይጄሪያ በቅርቡ በትራምፕ ትችት ደርሶባታል። ትራምፕ  እዚያ ያሉ ክርስቲያኖች በእስላማዊ ታጣቂዎች እየተሳደዱ እንደሆነ እና መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም በቂ ጥረት እንዳላደረገ ተናግረዋል። የናይጄሪያ ባለስልጣናት ግን አስተባብለዋል። ያምሆኖ ናይጄሪያ ባለፈው ዓመት ታህሳስ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰሜናዊ ምዕራብ ናይጄሪያ በሚገኙ ፅንፈኛ ሀይሎች በመሸጉባቸው ቦታዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች።ይህም የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ክስ ተከትሎ ነው።በናይጄሪያ ቦኮ ሃራምን እና የምዕራብ አፍሪካ እስላማዊ ግዛትን ጨምሮ በተለያዩ የታጠቁ ቡድኖች ከፍተኛ ጥቃት ሲደርስ ቆይቷል።


ፀሐይ ጫኔ
እሸቴ በቀለ