የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዐቃቢያነ-ሕግጋት ከፊል የሥራ ማቆም አደረጉ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 11 2018
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዐቃቢያነ ህጎች ከፊል የሥራ ማቆም አደረጉ
በሸዋንግዛው ወጋየሁ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያክልል ዐቃቢ ህጎች ከፊል የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታወቁ ፡፡ አቃቢያነ ህጎች ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ በከፊል ሥራ ያቆሙት መንግሥት የፍትህ ሥርዓቱን ለማጎልበት የፈቀደው የአቃቢያነ ህግ የደመወዝ እና የጥቅማ ጥቅም ማሻሻያ ተግባራዊ አልሆነም በሚል ነው ፡፡ አቤቱታቸውን ተፈራርመው ለክልሉ መንግሥት ያመለከቱት ከ500 በላይ ዐቃቢያነ ህጎቹ ጥያቄያቸው እስኪመለስ ከመደበኛ ችሎት በስተቀር ከፖሊስ እና ከማረሚያ ቤቶች ጋር የሚሰሯቸውን ተጨማሪ የፍትህ ሥራዎች ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጣቸውን ገልጸዋል ፡፡
የአዋጁ ተፈጻሚ አለመሆን
ፊርማቸውን በማሰባሰብ አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት ያቀረቡት በክልል ፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ በማገልገል ላይ የሚገኙ አቃቢያነ ህጎች ናቸው ፡፡ አቃቢያነ ህጎቹ እንደሚሉት የክልሉ ምክር ቤት ባወጣው አዋጅ ቁጥር 3/2014 መሰረት የዓቃቤያነ ህጎችን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅምበልዩ ሁኔታ በዓቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ ተጠንቶ መቅርብ እንዳለበት ይደነግጋል ፡፡ ነገር ግን ይህ አዋጅ ተፈጻሚ ባለመደረጉ አሁን ላይ የሚገባቸውን የደመወዝ ማሻሻያ እና ጥቅማ ጥቅሞችን ማግኘት እንዳልቻሉ ነው ሁለት የሠራተኞቹ አስተባባሪ ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ፡፡
የክልሉ ዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ በአዋጁ መሰረት የወቅቱን የገበያ ሁኔታና ሌሎች አቻ ክልሎች አፅድቀው ተግባራዊ ያደረጉትን የደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም መነሻ በማድረግ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ማቅረቡን የጠቀሱት የዐቃቢያነ ህጎቹ አስተባባሪዎች “ ነገር ግን መስተዳድር ምክር ቤቱ ያለአንዳች አሳማኝ ምክንያት የቀረበውን ውድቅ በማድረግ በዘፈቀደ በራሱ የወሰነው ውሳኔ አዋጅ እና ደንብን የጣሰ፣ ለተቋሙ በተለያዩ ህጎች የተሰጠውን ከፍተኛ ኃላፊነት ያላገናዘበና ወቅታዊ የኢኮኖሚ ጫናን ታሳቢ ያላደረገ ነየገቢ አጠቃቀም ተግዳሮት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልው “ ብለዋል ፡፡
አዎንታዊ ምላሽ ይጠብቃሉ
ዶቼ ቬለ የአቃቢያነ ህጎቹ አቤቱታን አስመልክቶ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊን ቢጠይቅም የአቤቱታ ጥያቄው ለቢሮው ባልደረሰበት ሁኔታ አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡ የክልል ርእሰ መስተዳድር የህግ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዳግም ዳንኤል ስብሰባ ላይ ሥለሆንኩ እኔ ደውላለው ቢሉም እንዳሉት ሊደውሉ አልቻሉም ፡፡ ቢደውልላቸውም ስልካቸው ጥሪ አይመልስም ፡፡
የክልሉ መንግሥት ውሳኔውን እንደገና መርምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ አዎንታዊ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማ እንደሚሸጋገሩ የተናገሩት አስተባባሪዎቹ “ህጋዊና ተገቢውን ሂደት ተከትለን ያቀረብነውን ጥያቄ ባለመቀበሉ የተነሳ ተገድን በምንወስባቸው ውሳኔዎች ምክንያት በክልሉ ህዝብም ሆነ መንግስት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ሙሉ ኃላፊነት የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን “ ብለዋል ፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ